ሰላም ሰዎች ዛሬ አንድ ነገር እንድታማክሩኝ እፈልጋለሁ; ለ ቤተሰቤ የመጀመርያ ልጅ ነኝ(3 እህትና 1 ወንድም አለኝ) እና የ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነኝ አባቴ ለልጆቹ ጥሩ አባት ነው ሲያሳድገኝ ምንም እንዳይጎለኝ አድርጎ ነው። ግን ለናቴ ጥሩ ባል አይደለም ነፍስ ካወኩ ጀምሮ አንድም ቀን በሰላም ውላ አታወቅም 22 አመት ሙሉ የውሸት ሳቅ እየሳቀች ለልጆቿ ስትል እየኖረች ነው፣ አባቴ ከልጆቹ ፊት ሲያመናጭቃት ሊመታትም ሲሞክር ማየት ለ 6 አመቱ ወንድሜ ብርቅ አይደለም፣ እኔ ቤት ስላልሆንኩ ሚገላግሉ እነሱ ናቸው። አላውቅም ለምን ለእናቴ ፈጣሪ አባቴን እንዳገናኛት። አሁን ያስጨነቀኝ ጉዳይ ታናናሾቼ እዛ ምግብ እንጂ ፍቅር የሌለበት ቤት ሲኖሩ በልጅነታቸው እንዳይጎዱብኝ ቀን በቀን እሰጋለሁ፧ ምከንያቱም ታናናሾቼ እኔ የደረሰብኝ እየሆነባቸው ነው እኔም በዛ ምክንያ ትምህርቴ እየሰነፍኩ ነው፣ እባካችሁ ምን ላድርግ ምከሩኝ🥺
Mar 18, 2025Yhe awttew baynagerutm ye abzagnochachn guada asazagn mistr new. Ene mmekrh tmhrthn wetreh chers, sra jemrna dreslachew, kechalkm antega anurachew. Ahun betemarinet akm mn zelaki neger mamtat ychalal.
Mar 18, 2025