እውነተኛ ደስታ ማግኘትየሚቻለው እንዴት ነው?
አንድ የቡዲዝም ሃይማኖታዊ መሪ የሆኑ ዳላይ ላማ“የሕይወታችን ዋነኛ ዓላማ ደስታ ማግኘት ነው ብዬ አምናለሁ”ሲሉ ተናግረዋል። ከዚያም አእምሮንና ልብን በማሰልጠን ወይምበመገሰጽ ደስታ ማግኘት ይቻላል ብለው እንደሚያምኑ አብራሩ።“አእምሮ” ይላሉ ሃይማኖታዊ መሪው “የተሟላ ደስታለማግኘት የሚያስፈልግ ብቸኛ መሣሪያ ነው።” እኚህ ሰውበአምላክ የማመኑ አስፈላጊነት አይታያቸውም።a
ከዚህ በተቃራኒ ግን በአምላክ ላይ ጠንካራ እምነት የነበረውንናበትምህርቱ ላለፉት ብዙ መቶ ዘመናት በመቶ ሚልዮንየሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት የነካውን ኢየሱስን ተመልከት።ኢየሱስ የሰው ልጆች ደስተኛ እንዲሆኑ ይፈልጋል። ዝነኛየተራራ ስብከቱን የጀመረው ደስተኛ ስለሚያደርጉ ዘጠኝ ነገሮችበመግለጽ ነው። (ማቴዎስ 5: 1-12) በዚሁ የተራራ ስብከቱ ላይአድማጮቹ ከሥነ ምግባር ውጭ የሆኑትን እንዲሁምዓመፀኛነትና ራስ ወዳድነት የሚንጸባረቅባቸውን አስተሳሰቦችሰላማዊ፣ ንጹህና ፍቅራዊ በሆኑ ሐሳቦች በመተካትአእምሮአቸውንና ልባቸውን እንዲመረምሩ፣ እንዲያጠሩናእንዲገስጹ አስተምሯቸዋል። (ማቴዎስ 5: 21, 22, 27, 28፤ 6: 19-21) ከኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መካከል አንዱ ቆየት ብሎእንዳሳሰበው “እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፣ ጭምትነትያለበትን ነገር ሁሉ፣ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፣ ንጹሕየሆነውን ነገር ሁሉ፣ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፣ መልካም ወሬያለበትን ነገር ሁሉ፣ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን” እንዲህያሉትን ነገሮች ማሰባችንን መቀጠል ይኖርብናል። —ፊልጵስዩስ4: 8
ኢየሱስ እውነተኛ ደስታ ከሌሎች ጋር ያለንን ግንኙነትእንደሚነካም ያውቅ ነበር። እኛ ሰዎች በተፈጥሯችን ከሌሎችሰዎች ጋር መቀላቀል እንወዳለን። ስለዚህ ራሳችንን የምናገልልወይም ከምናገኛቸው ሰዎች ጋር ሁልጊዜ የምንጋጭ ከሆነእውነተኛ ደስታ ሊኖረን አይችልም። ደስተኛ መሆን የምንችለውየምንወደድ ሆኖ ከተሰማንና እኛ ራሳችን ሌሎችን የምንወድከሆነ ብቻ ነው። ኢየሱስ እንዳስተማረው ደግሞ እንዲህ ላለውፍቅር መሠረቱ ከአምላክ ጋር ያለን ዝምድና ነው። ኢየሱስሰዎች ከአምላክ ርቀው በራሳቸው ቢመሩ እውነተኛ ደስታእንደማያገኙ በማስተማር ከዳላይ ላማ የተለየ አመለካከትእንዳለው አሳይቷል። ይህ የሆነው ለምንድን ነው?
Mar 18, 2025