ለጋስነት በልቤ ውስጥ ተዘርታለች:የሕይወት እጣ ለጋስ እጆቼን ብታስርበኝ ሞትን እመርጣለሁ። ጥበብን የምሻ ነኝና መለገስ ካልቻልኩ ፈፅሞ አልቀበልም። የሰው ልጅ ቁጣ እንደ አውሎ ነፋስ ያጓራል። እኔ ግን በዝምታ እተነፍሳለሁ፡፡ ምክንያቱም ትንፋሼ ፈጣሪ ጋር ሲደርስ ወጀቡ በሙሉ ይቆማልና። ሰዎች ምድራዊ ነገሮች ላይ ይንጠለጠላሉ፡፡ የኔ መሻት ግን የፍቅር ችቦ ናት። በብርሃኗ የልቤን ሰብአዊነት ታነፃልኛለች፡፡ ሰዎች በዘር ፣ በቀለም በሃይማኖት ተከፋፍለዋል። እኔ ደግሞ በሁሉም አገር እንግዳ ነኝ – የየትኛውም ወገን አይደለሁም፡፡ ሥነ-ፍጥረት (ዩኒቨርስ) አገሬ ስትሆን ጉሳዬ ደግሞ ሁሉም የሰው ልጅ ነው፡፡ የሰው ልጅ አቅመቢስ ሆነውም የተከፋፈሉ ናቸው። በየጊዜው የምትጠበውን ምድር በግዛትና አገራት መሰነጣጠቅ አላዋቂነት ነው። የሰው ልጆች እጅ ለእጅ የሚያያዙት የነፍስን ቤተ መቅደስ ለማፍረስና ምድራዊ ድልድይ ለመገንባት ብቻ ነው። ብቻየን ቆሜ እንዲህ የሚል የውስጥ ድምፄ ተሰማኝ ፡ #ፍቅር ለሰው ልብ ሕይወት እንደምትሰጥ ሁሉ አለማወቅን ማወቅ ደግሞ የእውቀትን መንገድ ያሳየዋል። ፍቅርና አለማወቅን መረዳት ወደ ታላቅ ደስታ ይመራሉ– ምክንያቱም ፈጣሪ ከፀሀይ በታች ለሰው ልጅ መከራን አልፈጠረምና። የ እናንተ የኑረት መርሀችሁ ግን ምንድን ነው? Live Life To-The Fullest-To The Maximum Level
Mar 17, 2025የሰላሞቼ እመቤት 😂
Mar 17, 2025