ሰዎች በጣም ግራ ስላጋባኝ ነገር ልንገራችሁ .... እናት እና አባቴ በትዳር 23 አመት ቆይተዋል በጣም ደስ የሚል ቤተሰብ ነው ያለኝ ። ፍቅራቸው አሁንም ድረስ አለ ።አንዳንዴ ሲጣሉ የፀባቸው ምክንያት እናቴ ነው የምትሆነው እና ብዙ ጊዜ አባቴ ያማክረኛል ። ተመካክረን እናቴንም ተቆጥቼ ችግሩን እፈታዋለሁ ። እና አሁን ላይ እነሱ የሚያጋጫቸው ምክንያት እኔ ከፍቅረኛዬ ጋር የምጣላበት ምክንያት ሆኖ አገኘሁት ። በእኔ እና በፍቅረኛዬ ህይወትም ፀብ የምፈጥረው እኔ ነኝ እንደ ማይወደኝ እንደ ማያከብረኝ እንደ ማይፈልገኝ ይሰማኛል ያ ልክ እንዳለሆነ እያወኩ እንኳን ውስጤ negative ነገር ሲያስብ አዳምጠው እና ከፍቅረኛዬ ጋር እከራከራለሁ እጣላለሁ ። እሱም ይሄን ነገር ስለሚረዳኝ ተረጋግቶ ያናግረኛል ይሄ ትክክል አደለም ፀሎት አርጊ ውስጥሽ መጥፎ ነገር ሲያስብ አስቁሚው አትስሚው እያለ ይመክረኛል እኔም ለማሻሻል እየጣርኩ ነው በዚህ መሀል እናቴ እንደዚህ እየተሰማት እንደሆነ አባቴ ምከሪያት እስቲ አለኝ ....ብቻ ስሜቱን ስለማቀው ደበረኝ እና ደሞ ግራ አጋባኝ መፍትሔው ምን ይሆን😢
Mar 16, 2025Tadelsshe sele betsebochsh❤️
Mar 17, 2025