Why are we told not to question everything that is written in the Bible or doubt anything that is said in church?
Oct 11, 2020I am sorry to say this but who ever said that to you doesn't know the Bible........ the bible doesn't say Donot ask rather it say "ask every thing" ........ ግን ደግሞ ዝም ብሎ በጭንቅላትህ ያለፈውን ሁሉ ተመራምረህ አትችለውም፣ እና ደግሞ የመጣውን የሳይንቲፊክ ምርምር ሁሉ ከ መፅሃፍ ቅዱስ ጋር አስታርቃለሁ ማለት የለብህም። ምክንያቱም ሳይንስ በመሰረቱ ህፁፅ የሆነ ወይም ፍፁም ያልሆነ ነገርን ብቻ ነው መመርመር የሚችለው እና ደግሞ ሁል ጊዜ አንድ እውነት ነው ብሎ የተቀበለው ነገር (premise)ያስፈልገዋል so technically science by it self is a logical belief......... ምክንያቱም premise ስህተት ከሆነ conclusionኑም ስህተት ስለሚሆን ስለዚህ ያጠራጠረህን መርምር፣ ጠይቅ ተረዳ እንጂ ዝም ብለህ ስህተት ነው አትበል!!! ችግሩ ብዙ ጊዜ ሰው የሚጠይቀው ለማወቅ ሳይሆን ለመቃወም(challenge) ለማድረግ መሆኑ ነው ........ ለምሳሌ ከ Louis pasture ዘመን በፊት ሰዎች በ "spontaneous generation of living thing" ያምኑ ስለነበር ሥነ-ፍጥረት ራሱን በራሱ አስገኘ በማለት ይከራከሩ ነበር። ግን ያንን theory Louis Pasture ስህተት መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ አሁንም ድረስ ብዙ atheists እንደዛ ብለው ይከራከራሉ ሌላም ምሳሌ ብንወስድ "the law of entropy" "ጥቅም ላይ የሚውል ኃይል ወይም (usable energy) ውስን እና የሚያልቅ ነው ይላል" ....... ግን አሁንም በስነ-ፍጥረት ዘልዓለማዊነት(eternity of universe) የሚያምኑ ሳይንቲስት ተብለው የሚጠሩ ብዙ ናቸው እና ሳይንስን አጣመው በሳይንስ ስም የatheism እምነትን የሚያስተምሩትን ሁሉ እውነት ነው እያልክ መፅሐፍ ቅዱስ ትክክል አይደለም አትበል ሌላው ከመፅሐፍ ክፍል ያልገባህን ጠይቅ እንጂ አውዱን ሳትረዳ ለመቃወምም አትቸኩል እዚህ ጋር the baker Baker paradoxን ላንሳ ( ጥናቱ የሰውን የማስታወስ እና የማያያዝ አቅም ለማጥናት የተደረገ ነው ግን እኔ እንዲመቸኝ አድርጌ ላቅርበው) አንድ ሰው ወደ ክፍል ገብቶ "እኔ Baker ነኝ" አለ ስለዚህ አድማጭ ቁጥር 1 ሰውየው ስሙ "ቤከር" ነው ብሎ ተረዳ አድማጭ ቁጥር 2 ደግሞ ሰውየው "baker" ወይም ዳቦ ጋጋሪ ነው ብሎ ተረዳ ከዚህ በኋላ ትንሽ ቆይቶ ተናጋሪው ሰውዬ ስራዬ ህክምና ነው ቢል አድማጭ ቁጥር 2 ከአውድ ውጭ ስለተረዳ ሰውየው የዋሸ ወይም እርስ በራሱ የተጋጨ ንግግር የተናገረ ሊመስለው ይችላል። እሱ ስላልተረዳው ግን ሰውየውን ውሸታም አያረገውም ግን በትክክል ቢረዳ ሰውየው ስሙ ቤከር እንደሆነ እና ስራው ሐኪም እንደሆነ መረዳት ይችል ነበር ስለዚህ መፅሐፍ ቅዱስን ራሱን መፅሐፉን ብቻ ሳይሆን ታሪኩን፣ የሚነሱበትን ጥያቄዎች እና የተሰጣቸውን መልሶች፣ ትርጓሜውን ወዘተ ካነበብክ ያኔ በደንብ ትረዳዋለህ። እና ለሁሉም ፈጣሪ ከሰማይ ሆኖ "ሀ ሁ..." እያለ ምድራዊውን ሁሉ ያስተምረኝ እንደማትል ሁሉ ሳይንስም እዚህ ሆኖ ከscope ውጭ የሆነውን የፈጣሪን ነገር ሁሉ ያስተምረኝ አትበል እንጂ ...... መመራመር እና ማወቅ አይከለከልም አመሰግናሁ!!! እና ስላረዘምኩት ይቅርታ
Oct 16, 2020