ሰላም እስኪ የራሳችሁን ሀሳብ አጋሩኝ _Low of attractin ወይም አንድን ነገር አብዝተን ስንፈልገው ወደኛ ይቀርባል ወይስ በጣም በፈለግነው ቁጥር ከኛ ይርቃል ወይም እንዳባባሉ የፈሩት ይደርሳል እንደሚባለው ማለት ነው በየትኛው ነው ምታምኑት?
Mar 14, 2025ስለ ስበት ህግ የተዘመረለት The Secret የሚለው የ Rhonda Byrne መፅሐፉ በ hard copy አለኝ። እኔ መፅሐፍ ማንበብ ጀምሬ አላቋርጥም። The Secret የሚለውን ይሄን ውል አልባ የፍልስፍና መፅሐፍ ግን ግማሽ ያክል እንኳን ለማንበብ አልቻልኩም። የማይጨቀጥ ነገር ነው የሚዘረዝረው። አንድ ምሳሌ ልስጥህ ሁላችንም ገንዘብን አጥብቀን እንፈልገዋለን። ስለ ፈለግነው ብቻ ገንዘብ ወደ እኛ ዝር አላለም😑 ። ዳዊት ድሪምስ ንግግሩ ውሃ የማያነሳው የስበት ህግን ፍልስፍና ሳያላምጥ በመዋጡ ነው። አዎንታዊ አስተሳሰብ ሊኖረን እንደሚገባ ሳይታለም የተፈታ ሆኖ ሳለ ይሄ እሳቤ ብቻውን የውስጣችንን ጥያቄ ይመልሳል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። በአጭሩ ከዕውነታ የራቀ ፍልስፍና ነው። Personal view!
Mar 14, 2025