Sle condominium bzwum alawulkm gn real estate kefelek gn egna ga ale century real estate DM: @Tadiwes16 Or 📱: +251988031917
Mar 14, 2025Sle condominium bzwum alawulkm gn real estate kefelek gn egna ga ale century real estate DM: @Tadiwes16 Or 📱: +251988031917
Mar 14, 2025የኮንዶሚኒየም ቤትን በወለድ አግድ ማስያዝ ----- - - - ኮንዶሚኒየም ቤትን በተመለከተ በአ/አ ከተማ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 19/97 አንቀፅ 14(2) መሰረት የኮንዶሚኒየም ቤት ዕጣ የደረሰው ሰው ዕጣው ከደረሰው ቀን አንስቶ እስከ አምስት ዓመት ድረስ ለ3ኛ ወገን በሽያጭ ወይም በስጦታ ለማስተላለፍ እንደማይቻል በመደንገጉ ምክንያት አምስት ዓመት ሳይሞላው ኮንዶሚኒየም ቤቱን መሸጥ የሚፈልጉ ባለቤቶች በተለምዶ አሰራር የቤቱ ገዢ እንደ አበዳሪ በመሆን የቤቱ ሻጭ ደግሞ እንደ ተበዳሪ በመሆን፣ የኮንዶሚኒየም ቤቱ ደግሞ እንደ የብድሩ መያዣ ተደርጎ የመያዣ ውል ብለው ይፈራረማሉ፡፡ ይህ ውል በህግ ፊት ያለው ተቀባይነት ምን ይህል ነው የሚለውን ከማየታችን በፊት ስለ ወለድ አግድ ውል የተወሰኑ ነጥቦችን እንመልከት፡፡ - ወለድ አግድ( Antichresis) ማለት በፍ/ብ/ህ/ቁ 3117 መሰረት አንድ ባለዕዳ ላለበት ዕዳ አፈፃፀም ማረጋገጫ ይሆን ዘንድ ለባለገንዘቡ የማይንቀሳቀሰውን ንብረቱን የሚያስረክብበት፣ በአንፃሩ ባለገንዘቡ ከባለዕዳው ወለድ የማይጠይቅበት ውል ሲሆን ሊመሰረትም የሚችለው በውል ስምምነት ብቻ ነው፡፡ የወለድ አግድ ውልን ከመያዣ ውል የሚለው አንዱ ባህሪ በመያዣ ውል ላይ በዋስትና የተያዘው የማይንቀሳቀስ ንብረት በባለዕዳው ዕጅ የሚቆይ ሲሆን በወለድ አግድ ግን በዋስትና የተያዘው ንብረት በባለገንዘቡ ይዞታ ስር ወይም ባለዕዳው የማይንቀሳቀሰውን ንብረት አስረክቦት ባለገንዘቡ ይጠቀምበታል ማለት ነው፡፡ እዚህ ጋር በሁለቱ ውሎች መካከል ያለው መሰረታዊ ልዩነት መያዣውን ያቋቋመው የማይንቀሳቀስ ንብረት በማን እጅ ይቆያል የሚለው መሆኑን መገንዘብ እንችላለን፡፡ - የወለድ አግድ ውል እንደ መያዣ ውል ሁሉ በፅሁፍ ተደርጎ በሚመለከተው አካል ፊት ቀርቦ መመዝገብ ያለበት ሲሆን የወለድ አግድ ውልን ለማቋቋም የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣን መቋቋም የሚመለከቱት ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት እንዳላቸው በፍ/ብ/ህ/ቁ 3118 ተደንግጎ ይገኛል፡፡ የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ውል የሚያቋቁሙትን ድንጋጌዎች ስንመለት ደግሞ( አንቀፅ 3045፣3052 እና 3053 ይመለከተዋል) ይህ ውል ከተደረገበት ቀን ጀምሮ በማይንቀሳቀስ ሀብት መዝገብ ካልተፃፈ( ካልተመዘገበ) ምንም ዓይነት ውጤት እንደሌለው ተደንግጎ እናገኛለን፡፡ ይህንንም በማፅናት የፌ/ጠ/ፍ ሰበር ሰሚ ችሎት በቅፅ 10 መዝገብ ቁጥር 45422 እና በቅፅ 21 መዝገብ ቁጥር 117953 አስገዳጅ ውሳኔን ሰጥቶበታል፡፡ ከላይ የተነሳው የኮንዶሚኒየም ሽያጭ መንገድ በተለምዶ ሰዎች የመያዣ ውል ወይም የብድር ውል ይበሉት እንጂ ውሉ የወለድ አግድ ውል ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ደግሞ በተግባር የሚስተዋለው እና ገዢ እና ሻጭ መስማማት አቅቷቸው ጉዳዩ ወደ ፍ/ቤት ሲያመራ የሚነሳው ጭቅጭቅ ውሉ ወለድ አግድ እንደ መሆኑ መጠን በህግ የተቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ አሟልቷል ወይስ አላሟላም የሚለው ነው፡፡ ባለዕዳና ባለገንዘብ ብዙ ጊዜ ይህንን ውል በፅሁፍ ቢያደርጉም በሚመለከተው አካል ፊት ቀርበው ውሉን ስለማያስመዘግቡ ውሉ ፈራሽ ተደርጎባቸው ለእንግልት ሲዳረጉ ይታያል፡፡ ስለሆነም በኋላ ከሚመጣ እንግልት ለመዳን እና በህግ ፊት ተቀባይነት ያለውን ግዴታና መብት ለመመስረት ወለድ አግድን በተመለከተ ውሉ በፅሁፍ ሊደረግ እንደሚገባ እና ስልጣን ባለው አካል ፊት ተደርጎ ሊመዘገብ እንደሚገባው እንመክራለን፡፡
Mar 13, 2025