ሰላም፣ በቅርቡ አንድ ማየት የተሳነው ቤተሰቤ ጋር እያወራን የተለያዩ መጽሓፍት በፍላሽ አድርጎ በጂፓስ እና በላፕቶፑ እንደሚያዳምጥ እና በአውድዮ ማግኘት ግን በጣም እንደሚቸገር ነገረኝ። በተለይ የሀይማኖት መጽሓፍት ይፈልጋል። እኔ ፕሮቴስታንት ስሆን እሱ ግን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነው። መዝሙረ ዳዊትን በግዕዝ እና በአማርኛ ዩትዩብ ላይ አግኝቼ ባወርድለትም፣ መጽሓፍ ቅዱስ ግን እሱ የሚፈልገውን ሰማንያ አንድ አሀዱ በአማርኛና በግዕዝ ማግኘት አልቻልኩም። ከፒዲኤፍ መጽሓፍ ላይ የሚያነብለት ላፕቶፕም አለው። ግን ሶፍትዌሩ ስካን የተደረገ ነገር ሲሆን ማንበብ አይችልም፣ እናም ስካን ያልተደረገ መጽሓፍ ቅዱስ እና ሌሎች የሀይማኖት መጽሓፍት እና ፣ አውድዮ መጽሓፍት(የተዋህዶ) ያላችሁ ወይም ኦንላይን ማግኘት የምችልበትን ቦታ መጠቆም የምትችሉ 🙏🙏🙏 ብትልኩልኝ ትልቅ እርዳታ ይሆናል።
Mar 13, 2025ለመጀመሪያ ጋዜ rational Protestant ሳይ 👏👏👏
Mar 13, 2025