Selam endet nachu wid Christian och / Orthodox , Protestant , Catholics / 1 tyake lityikachu nbr diaconat, pastoroch kallachihu melsulign Amilakachin geta eyesus kerstos ke 3 tum haymanotch wst endalnbr yitawekal so enezi haymanotoch keyet metu man feterachew esu endezi bilachu tekefafelu alalenm kaltesasatiku be metshiaf kidus tirugame liyunet ena aredad yetftru yimesilegnal 1 sew ke enezi haymanotoch wst sayhon egziabhern mamilek aychilm? Ye gid haymanot linorew yigebal? Lik ende hawariayatu be kerstos amno menor aychilm?
Mar 12, 2025የሃዋርያትን ቤተክርስቲያን የግድ መከተል አለብህ እውነተኛ እየሱስን ለመከተል። ቤተ ክርስቲያን ሲባል በመጀመርያ ተቋም አድርገሽ አትመልከተው የሰዎች ስብስብ ነው። መጀመርያ ክርስቶስ እና ሃዋርያት ነበሩ ክርስቶስ ሄደ ከዛን ሃዋርያት ስራ ጀመሩ እያስተማሩ (በቃልም በፅሁፍም) እና እያጠመቁ ሰዎችን ወደ ህብረታቸው እየቀላቀሉ መጡ ወደ ክርስቶስ ማለት ነው። ይህ ህብረት ደግሞ አንድ ህብረት ነው። ህንፃ ቤተክርስቲያናት እየተገነቡ መጡ። ክርስትና ማለት ህብረቱ እንጂ ህንፃው ወይም ተቋሙ አስተዳደሩ አይደለም ስለዚህ ክርስቲያን ለመሆን ከሌሎች ክርስትያኖች ጋር ህብረት መፍጠር አለብህ ጥያቄው ትክክለኛው ህብረት የትኛው ነው ነው? ታሪክን በደንብ መረዳት አለብህ። ሀዋርያቶች የሰሩት ህብረት እነሱ ካለፉ ከሆኑ አመታት ቦሀላ መከፋፈል ጀመሩ። በጥቂት አስተምሮዎች እና አረዳዶች አንዳንዶቹ ከሀዋርያት አስተምህሮ ያፈነገጡ አንዳንዶቹ ደግሞ በሰዓቱ የነበሩ የሃዋርያት ሃዋርያት ሁሉ ግራ የሚያጋቡ ምልከታዎች ይነሱ ነበር። እየዋለ እያደረ በቀኖና እና ዶግማ በትውፊትም በስርዓትም ሰው ከሰው እየተለያየ እየተከፋፈለ መጣ። ወንድሜ በመሰረቱ መፅሀፍ ቅዱስን ብቻዬን አንብቤ መኖር እችላለው ማለት ከባድ ነው። ምናልባት አንተ ራስህ አዲስ የመፅሀፍ ቅዱስ አረዳድ ይዘህ ትመጣ ይሆናል። ይሄ ሁሉ ልዩነት የተፈጠረው የተለያዮ ሰዎች በመፅሃፍ ቅዱስ ላይ ያላቸው እምነት በመለያየቱ ነው። የተለያዩ ሀይማኖቶች እንዲፈጠሩ ያደረጉት ሁሉም መሰረታቸው ክርስትና ነው እየሱስ ነገር ግን እይታዎች አረዳዶች ትልቅ ልዩነት ፈጠረና እንዲ ተከፋፈሉ so መፅሀፍ ቅዱስን በሁሉም አረዳድ ለመመልከት ሞክር የትልልቀቅ አባቶች እይታ ደግሞ ለዚህ ይረዳሀል። በተለይ በተለይ ትልልቅ conference በደንብ አጥና እንደ የኢየሩሳሌም ጉባዔ የኤፌሶን ጉባዔ የኒቂያ ጉባኤ የኬልቄዶን ጉባዔ የቁስጥንጥንያ ጉባዔ የመፅሀፍ ቅዱስ ብዛት (ቁጥር) የመፅሀፍ ቅዱስ ይዘት እና የመፅሀፍ ቅዱስ አረዳድን ከጥንት ጀምሮ እንዲለያይ ያደረጉ ግለሰቦች እና ጉባዔያት አስተምህሮ deeply ተመልከት ያኔ ትክክለኛውን ህብረት ታገኘዋለህ። ሀይማኖትን በስርዓት እና ትውፊት እንዳትመዝን። በመጨረሻም እውነተኛይቱንና ትክክለኛ የእግዚአብሔር ህብረት ያለባት ቤተክርስቲያን ታገኛለህ። ተስፋ እንዳትቆርጥ
Mar 13, 2025