Hey guys so i am not orthodox but curious to know what ፍትሀት is yk when they die ena demo sew erasun katefa lemn endmayderglet eski asredugn
Mar 12, 2025ፍትሃት ማለት ከዚህ አለም በሞት ለሚለያዩት ሰዎች በህይዎተ ስጋ ሳሉ ከሰሩት እና ከፈፀሙት በደል እንዲነፁ ከማእሰረ ሃጢአት እንዲፈቱ ወደ እግዚአብሄር የሚቀርብ ፀሎት ነው፡፡ቤተክርስቲያን ለሙታን ፀሎተ ፍትሃት እንዲፈፀም ታዛለች፡፡ ፀሎተ ፍትሃት ለበድሉት ስርየተ ሃጢአትን ይቅርታን እረፍተ ነፍስን ያሰጣል፤ ለደጋጎች ደግሞ ክብርን፣ ተድላን ፣ እረፍትን ያስገኛል፡፡ ሙታን እና ህያዋን የሚገናኙት በፀሎት አማካኝነት ነው፡፡‹‹ህያዋን ለሙታን ይጸልያሉ፤ ሙታንም ለህዋን ይለምናሉ››ሄኖ 12፣34 ህያዋን ለሙታን የሚያቀርቡት ፀሎት እና መስዋእት በግልፅ እንደሚታይ ሁሉ ሙታንም በአጸደ ነፍስ ሆነው በዚህ አለም ላሉ በንስሃ ሳይመለሱ እንዳይሞቱ ይለምናሉ፡፡ ፀሎተ ፍትሃት የሚደረገው በሃይማኖት ለፀኑ ሰዎች ነው። ማቴዎስ 12 (Matthew) 32፤ በሰው ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም ቢሆን ወይም #በሚመጣው አይሰረይለትም። #በሚመጣው ዓለም በጌታ መምጫ ይቅርታ የማይደረግለት ሰው በመንፈስ ቅዱስ ላይ የተሳደበ እንደሆነ ተነግሯል ይህ ማለት በዚያን ቀን ይቅርታን የሚያገኝም እንዳለ ደግሞ ትልቅ ማሳያ ነው.. ስለዚህም በዚያች በፍርድ ቀን ይቅርታ ተደርጎላቸው ሊማሩ የሚችሉ ክርስቲያኖች አሉ.. ይህ እንዲሆን ግን እኛ እዚህ ልንፀልይላቸው ይገባል.. የሞቱ ቤተሰቦች ቢኖሯቹ ስለ እነሱ ብጺለይ የማይሰማ ጌታ የለንም.. የመጨረሻው ፍርድ እስኪመጣ ድረስ በዚህ መልኩም የጌታን ምህረት ማጣጣም ይቻላል.. በፍርድ ቀን ደግሞ ጌታ እርሱ ያቀልላቸዋል ማለት ነው.. ማቴዎስ 11 (Matthew) 24፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ #በፍርድ_ቀን ከአንቺ[ከቅፍረናሆም] ይልቅ ለሰዶም አገር #ይቀልላታል። "ከሞቱ ሞቱ ነው ምንም ተስፋ የለም" በሚል የአጋንንት ድምፅ እንዳንዘናጋ.. ጌታ የነገረን ሌላ ነው.. 2 ጢሞቴዎስ 1 (2 Timothy) 18፤ #በዚያን_ቀን_ከጌታ_ምሕረትን_እንዲያገኝ_ጌታ_ይስጠው፤ በኤፌሶንም እንዴት እንዳገለገለኝ አንተ በደኅና ታውቃለህ። #በዚያን_ቀን መቼ..?? እንዲህ ተብሎ የተነገረለት ሰው በሰዓቱ እንደሞተ በብዙዎች የታመነ ነው.. ባይሞት እንኩአን በዚያን ቀን ማለቱ ለምን አስፈለገ ያልን እንደሆነ የመጨረሻው ፍርድ ላይ የተለየ ነገር ስለሚኖር ነው.. #ራሱን ላጠፋ ሰው ለምን ፍትሃት አይደረግለትም ? ቤተ-ክርስቲያን ለሃጢአት ስርየት ፀሎት የምታደርገው ሞት ለሚገባው ሀጢአት ሳይሆን ሞት ለማይገባው ዘላለማዊ ሕይወት ነው፡፡1ዮሃ 5፣16 ለምሳሌ በተለያየ ምክንያት ራሱን ያጠፋ ሰው ፍትሃት አይደረግለትም፡፡ ምክንያቱም ቤተ መቅደስ ሰውነቱን አፍርሱአል እና ‹‹.....ማንም የእግዚአብሄርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሄር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና ያውም እናንተ ናችሁ›› 1ቆሮ6፣14 ቤተ-ክርስቲያን ፍትሃት የምታደርገው በፍፁም እምነት ነው፡፡ ሐዋርያው ዮሃንስ ‹‹ሞት የሚገባው ሃጢአት አለ፤ስለዚህ እንዲጠይቅ አልልም፤....››እንዳለ ቤተ-ክርስቲያንም የምትከተለው ይህንን ነው፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሄረር እድሜ ለንስሃ ሰቱዋቸው ንስሃ ሳይገቡ፣ ስጋ ወደሙ ሳይቀበሉ በእግዚአብሄር ቸርነት እየቀለዱ የሚኖሩ አሉ፡፡ እነዚህ በራሳቸው የፈረዱ ናቸው፡፡ደግሞም ስሞት በጸሎተ ፍትሃት ሃጢአቴ ይሰረይልኛልና ሃጢአቴን አልተውም ማለት በእግዚአብሄር መሃሪነት መቀለድ እና እርሱንም መደፋፈር ስለሆነ ይህ ሞት የሚገባው ሃጢአት ነው፡፡ ነገር ግን ማንኛውም የቤተ-ክርስቲያንን ሚስጥራት ሲካፈል የቆየ እና በድንገት በአደጋ ምክንያት ያረፈ፣በ በርሃ የወደቀ፣ በአውሬ የተበላ ምእመን ምንም እንኩዋ ፀሎተ ፍትሃት ባይደረግለትም ቤተ- ክርስቲያን በጥቅሉ ስለ ሙታን ዘወትር በጸሎቱዋ ስለምታስብ ፀሎተ ፍትሃቱ በጋራ መፈፀሙ አይቀርም፡፡ቤተ-ክርስቲያን ሁሌ ስለ ሙታን ትፀልያለች፡፡
Mar 12, 2025