#URGENT Does anybody have "tsegereda" poem by Kebede Mikael please it's really urgent
Mar 09, 2025ፅገሬዳ እና ደመና የፀሀዩ ንዳድ ያጠቃት በብዙ ጠውልጎ የሚታይ የቅጠሏ ወዙ አንዲት ፅገሬዳ ቃሏን አስተዛዝና እንዲ ተናገረች ለሰማይ ደመና ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ድርቀት በጣም ጎድቶኝ እየኝ ስንገላታ እባክህ ጣልልኝ የዝናብ ጠብታ ቶሎ ካላራስከኝ ጉልበቴ እንዲጠና ምንም ተስፋ የለኝ መሞቴ ነውና አሁን መሄዴ ነው ለትልቅ ጉዳይ ስመለስ መጥቼ ሳልፍ ባንቺ ላይ እዘንብልሻለው ጠብቂኝ እያለ ደመና ጉዞውን ወደፊት ቀጠለ ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ጉዳዩን ጨርሶ ቆይቶ ሲመጣ ያቺ ፅገሬዳ ስሯ ውሀ ያጣ እንደዛ አስተዛዝና ጭንቋን ያዋየችው የፀሀዩ ንዳድ አድርቋት ቆየችው እስኪጎርፍ ድረስ የወንዝ ውሀ ሙላት ወዲያው እንደመጣ ዝናቡን ጣለላት ግን ደርቃለችና አልቻለም ሊያድናት ።።።።።። ሳልደርስላት ቀረው አዬ ጉድ እያለ ደመናም ጉዞውን ወደፊት ቀጠለ ሰውም እንደዚሁ ጭንቁን እያዋየ በችግሩ ብዛት እየተሰቃየ ጉዳዩን ጨርሶ ቆይቶ ሲጉላላ የሚረዳው አጥቶ ከሞተ በኋላ ዘመድ ወዳጆቹ እንባ እያፈሰሱ ተዝካር ቢያወጡለት አርባ ቢደግሱ ይህ ሁሉ ከንቱ ነው አይጠቅመውም ለሱ እውነት ከወደደው ሲቸገር ሲጎዳ 😉 በህይወቱ ሳለ ሰው ወገኑን ይርዳ ።።።።።።።።። ከበደ ሚካኤል 🏹 ።።።።አስታዋሽ : ዮርዳኖስ ሀይሉ ።።።። ጠቋሚ : አንተ ።።።።ፅገሬዳ እና ደመና እኛ የሰው ልጆች 😕
Mar 09, 2025