ጥያቄ ለሙስሊም ሴቶች Your boyfriend cheat ቢያረግብሽ ታዝኛለሽ? ምክንያቱም በእምነትሽ መሰረት ወደፊት አንቺን ጨምሮ 3፣4 ወይም ከዝያ በላይ ሚስቶች ሊኖሩት የሚችል ባል ለማግባት ፈቃደኛ ነሽ right? So what's your opinion?
Mar 06, 2025What a wicked viewpoint! ሴቷን ወክዬ ልመልስልህ.. የመጀመሪያ ሐሳብ በኢስላም boyfriend girlfriend የሚባል የዝሙት ጨዋታ አይፈቀድም። ሊያገባት የፈለጋት ሴት ካለች በክብር አባቷ ቤት ይሄዳል እንጂ በትዳር ስም የራሱ፣ የርሷን፣ የቤተሰቧንና የኢስላምን ክብር እንዲያጎድፍ አይፈቀድለትም። ሁለተኛ ሐሳብ (ዋናው ሐሳብ) በህጋዊ መንገድ ሽማግል ልኮ ሴቷን ከቤተሰቦቿ ቤት መውሰድና ያለቤተሰቦቿ ፈቃድ ከትዳር ውጭ አልጋ ላይ ማጋደም ይለያያሉ! ለነገሩ በናንተ ይህን መለየት አይቻልም። ግን ለያቸው። ለምሳሌ እኔ አንዲትን ሴት በትዳር የያዝኩ ብሆንና ተጨማሪ ሴት ብታስፈልገኝ ሚስቴ አወቀችም አላወቀች ያለ ሁለተኛ ትዳር ከሌላ ሴት ጋር ተኝቼ ብገኝ ያለ ጥርጥር ማግጬባታለሁ። በሸሪዐውም ህግ ተወግሬ እገደላለሁ። ነገር ያቺን ከሚስቴ ውጭ ያለችን ሴት ለመጀመሪያዪቱ የተከተልኳቸውን መስፈርቶች በመከተል ከቤተሰቦቿ እጅ ወስጄ ባገባት ሐላል ሆነችልኝ ማለት ነው። ምን ለውጥ አለው? የመጀመሪያው ያለ ህጋዊ የትዳር መያዣ መስመር መማገጤ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በህጋዊ መንገድ ከቤተሰቧ እጅ ወስጄ ማግባቴ ነው። ገባህ? በመሠረቱ አንድ ሰው ባገባቸው ሴቶች መሃል ፍትሐዊ ካልሆነ በአንድ እንዲብቃቃ ነው የታዘዘው። አንድ ወንድ ፍትሐዊ እስከሆነ ድረስ እስከ 4 እንዲያገባ የፈቀደና ካልሆነ በአንድ ብቻ እንዲብቃቃ ያዘዘው ኢስላም ብቻ ነው። ምድራዊ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ይህን ያህል አግቡ ብሎ ያዘዘ የ.ለ.ም! ሰማያዊው ቁርአን ግን አዞናል። ያው ትንሽ ከአእምሮህ ከፍ ብሎ ቢከብድህም ሰፋ ላድርግልህ ብዬ ነው። አንተ ባታነበው አንባቢ ያነበዋል። ጥያቄህን መልሼልሃለሁ። አሁን ደግሞ አንተ በተራህ መጣፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ወንድ በአንዲት ሴት እንዲብቃቃ የታዘዘበትን መ. ቅዳሳዊ ጥቅስ ጻፍልኝ። 1 ብቻ! 1 ብቻ!!! ከዚያ ግላዊ ሐሳቤን በመጣፋችሁ እሰነዝራለሁ። ከተራዊሕ ስመለስ ያንተን መልስ ነው የምጠብቀው።
Mar 06, 2025