Selam orthodox fam❤ ena 1teyake neberegn ena eskahun gelets selalhonelgn new lemnden new meskel weyem kir menaregew ena demo tabot be sew eji yetesera kehone lemn ensegedalen be honest melesulegn
Mar 04, 2025በግልጽነት መጠየቅሽ በጣም ጥሩ ነው❤️ በቻልኩት ለመመለስ ልሞክርና ማዕተብ ማለት"ዐተበ" ባረከ ከሚል የግዕዝ ቃል የመጣ ሲሆን በአንገታችንም ላይ የምናስረው ክሮች ተባርከው ስለምናደርጋቸው ማዕተብ ይባላሉ። በቤተ-ክርስትያናችን ውስጥ ነጭና ቀይ እንዲሁም ጥቁር ማህተብ ይደረጋል ✨የነጭና ቀይ ክር የሚደረግው በክርስትና ጊዜ ሲሆን ትርጉሙም ጥምቀተ ክርስቶስን የምናስብበት ነው ✨የጥቁሩ ማህተብ ምሳሌ ደግሞ በጥምቀት ባገኘነውን ክርስትና የምንቀበለውን መከራና ድካም ነው በዚህ ላይ ሌሎቹ ቤተሰቦች ይጨምሩበታል። _____ ልላው ለእግዚአብሔር የምንሰግደው ስግደት "የአምልኮ ስግደት" ይባላል ለቅዱሳን ሰዎች እና መላእክት፣ለቤተክርስቲያን፣ለታቦት(ለመሠዊያው)፣ቅዱሳን ሥዕላት ፊት የምንሰግደው ደግሞ "የጸጋ ስግደት" ወይም "የክብር ስግደት" ይባላል። የምንሰግድበት ምክንያት እና ያለን አስተሳሰብ ነው ዋናው ነገር እንጂ የአካላዊ እንቅስቃሴው መመሳሰል አይደለም። ለቅዱሳን ስንዘምርም እያመለክናቸው አይደለም በየትኛውም ለቅዱሳን እና ለመላእክት የምንዘምራቸው መዝሙሮች ላይ አምላኬ ፣ ጌታዬ ፣ ፈጣሪዬ ብለን አይደለም የምንዘምረው በተሰጣቸው ክብር ልክ ነው በዜማ የምናመሰግናቸው ይሄ ደግሞ በየትኛውም መለኪያ አምልኮ አይደለም። በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ታቦት ማለት ለዓለም ራሱን መሥዋዕት አድርጎ የሰጠ ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና ክቡር ደም የክብር ዙፋን (መሠዊያ) ነው፡፡ በታቦቱ ላይ የሚጻፈውም ቃልም "አልፋ ኦሜጋ" (ፊተኛውና ኋለኛው፣ መጀመሪያውና መጨረሻው የዘላለም አምላክ) የሚለው ቅዱስ ስሙ ነው(ራእ. 22፥13) ✍️በታቦቱ ፊትም የሚሰገደው ለዚህ ቅዱስ ስም ነው።
Mar 04, 2025