Anonymous
#business
ሰላም እንዴት ናችሁ ምን መሰላችሁ እኔ ጋርመንት እሰራ ነበር እና ምሰራው ትሸርት ነበር እና ልብስ ስፌት መስፋት እችላለሁ እና አሁን ያን ሥራ ጋርመቱን ትቼዋለሁ እና አሁን ላይ ሽፎን ቤት መስራት ፈልጌ ነበር ግን ያው መጀመሪያ ስራውን መልመድ ስላለብኝ ተቀጥሬ ማለት ክፍያ እንኩዋን ሳይከፈልኝ እየሰራሁ ሽፎን መስራት መለማመድ ነው የፈለኩት እና ለዛ ሚሆኑ ሽፎን ቤቶች ደግሞ እኔ ያለሁበት አካባቢ ጎንደር አዘዞ ሚባል ሰፈር በብዛት ብዙ ሽፎን ቤቶች አሉ ግን እኔ እነሱን ምን ብዬ አናግሬ መጠየቅ እንዳለብኝ አላቅም ማለቴ አሁን ላይ ሰው በሰው ካልሆነ በቀር ትንሽ ከባድ ነው እንደዚህ አይነት ሥራ ለመግባት እና እኔ ሚያስገባኝ ማለት አልቅም እና እንዴት መጠየቅ እንዳለብኝ እንድታማክሩኝ ነው
Jun 17, 20260 engagements