22 M neg talak wendme ke 6 amet befit mazer sew hager serta yemtamewatn genzeb be ቁማር,በመጠጥ,በሴት ቤት ውስጥ ለሚያስፈልጉ ነገሮች አላደርግ ብሎ እያስለቀሰን አራስ እህቴን ገና ታርሳ ሳትጨርስ እየደበደበ ማዘርን ደግሞ አንቺ ሸ** እና ብዙ ፀያፍ ቃል እየተሳደብ ብቻ ምን ልበላቹ ያኔ 24 አመቱ ነበር ለሀገር አስቸገረ እኔ ደግሞ 16 አመቴ ነበር ከዛ ማዘር ተሰቃይታ የምታመጣውን ብር ቤት አሰራለው ብሎ ሳያሰራ ብሯን ጨረሰው ከዛ ለኔ አደራ ብላ በኔ መላክ ጀመረች 1 ሳንቲም እንዳትሰጠው ብላ አስጠንቅቃኝ እኔን ደግሞ ላቤን እና ልፋቴን ቆጥረህ ቤቴን አሰራ ንብረት አፍራልኝ ብላ በኔ መላክ ጀመረች ከዛ መጀመሪያ ላይ እኔን እስከመግደል ሙከራ በኔ ላይ ማድረስ ጀመረ ሰዎች ናቸው ያተረፉኝ ብር ስከለክለው ከዛ አሁን30 ሊገባ ነው ስራ አይሰራም የሚኖረው የድሮ ቤታችን ነው ምግብ ብቻ ሊበላ ነው የሚመጣው ሲያየን ደሙ ይፈላል ይሳደባል ይራገማል አረቄ ይጠጣል ሲጋራ ያጨሳል እኔ ስለማያሳዝነኝ ትንሽ ትንሽ እያረኩኝ ብር ሰጠዋለው እሱን ሲጨርስ መልሶ ይሰድበኛል ያንቋሽሸኛል በመሀል ብዙ ስራ እንዲጀምር መንጃ ፍቃድ አውጥቶ ባጃጅ እንዲገዛለት ብዬ ሀሳቡን ጠየኩት አልፈልግም አለ ሙያ ላስተምርህ አልኩት እንቢ አለ እሺ ምንድነው ምትፈልገው ሲባል ብር ስጠኝ አለ እሺ ብለን ደብቄ የሆነ እቃ ተሽጦ ሲሰጠው 30kብር በአንድ ቀን አጠፋ 3 android ስልክ ያዝ ተጠቀም ብዬ ሰጥቼው በተለያየዘ ጊዜ ሁሉንም ሸጠ ጫማ እና ልብስ መግዣ ብዬ ሰጥቼው እነሱንም ሳይገዛ ብሩን አጥፍቶ በሲሊፐር ይመጣል እሺ እኔ ምን ላድርግ ገንዘብ ስለከለከልኩት ፈጣሪ ይፈርድብኛል??ጥፋተኛ ነኝ??ህሊናዬን እየወቀሰኝ ነው?ምን ላድርግ?እሱስ ምን ይሁን?
Jun 15, 2026Someone needs to intervene እንደተረዳሁት ከሆነ አቅም ያለው ሰው ኮስተር ያለ ትእዛዝ ሊያዘው ይገባል .እምቢ ካለ በጉልበትም ቢሆን ልክ ሚያስገባው ሰው መኖር አለበት አለበለዛ ሰላማዊ ኑሮ አይኖራችሁም.
Jun 15, 2026