"እኔ እሆንን" የሚለው መዝሙር ያላችሁ pleaseee lakulegn🙏🙏 ye zemarit sister hiwot teferi new
Feb 27, 2025እኔ እሆንን አላውቅህም ብዬ በሰው ፊት የምክድህ ለጠላት አንስቼ አሳልፌ የምሰጥህ እኔ እሆንን ጌታ ሆይ እኔ እሆንን እኔ እሆንን አምላክ ሆይ እኔ እሆንን ይሁዳ ነኝ ወይስ ጴጥሮስ ሀሙስ ማታ እኔ ማነኝ የዛሬን መቆሜን እንጂ አላውቅም መጨረሻዬን እወድሀለው ብዬ የዛሬን እናገራለሁ አላውቅህም እንዳልልህ ስለነገ ግን እፈራለሁ ስንት የአጥቢያ ኮከቦች ላንተ ዘሞረውልህ ወደቁ በሰማይ መቅደስህ አጥነው በትዕቢት ረግፈው አለቁ እፈራለሁ እኔም ለራሴ መንገዴን ንገረኝ ጌታ ጠዋት በዘመርኩበት አፍ እንዳልሳደብ በማታ ሳጥናኤል መልዐክ ነበረ ይሁዳም ሐዋርያ ንስጥሮስም ጳጳስ ነበር አርዮስም ባለሙያ እነዚህ ሁሉ ከወጡ ከአምላካቸው ጉያ ደካማ ለሆንኩትማ የት ይሆን የኔ መገኛ ታናሹን ጅማሪዬን አንተው ታላቅም አድርግልኝ ነበረች ከመባል ፈተና አንተው በፍቅርህ አድነኝ ያስጀመርከኝ አምላኬ ሆይ እንግዲህ መንገዴን አደራ በፊትህ ቆሜ ለማመስገን አብቃኝ ከቅዱሳን ጋራ https://t.me/Merkoryos25