#relationships እኔ ምላቹ 1 ሰው ከ እግዚአብሄር የተላከ መሆኑን እንዲሁም እግዚአብሄር የፈቀደው ግንኙነት እንደሆነ እንዴት ይታወቃል እስቲ በ እግዚአብሄር መልሱልኝ ምታቁ ሰዋች በጣም ግራ ገብቶኛል ከ 1 ሰው ጋር የፍቅር ግንኙነት አለኝ እና ድሮ ድሮ ነገሮችን ዝም ብዬም አልፍ ነበር አሁን ግን ብዙ አለቅሳለሁኝ በትንሽ በትልቁ እናደዳለሁኝ እንደ ፍቅረኛ ብዙም አይንከባከበኝም እሱን ብዬ እንጂ ብዙ ጊዜ ጥሩ ወንዶችን አግቼ ነበር ግን ፍቅር የያዘኝ ከሱ ጋር ነው ከ 2 አመት በላይ ሁኖናል እና እስቲ ልፀልይ እፈልጋለሁኝ እና እስቲ እንዴት ብላቹ ነው ምትለዩት እባካቹ እርዱኝ እድሜው እኩያዬ ነው 21 አመቴ ነው ሴት ነኝ By: Anonymous Status: Previewing
Feb 27, 2025ወደ እግዚአብሔር በጸሎት መቅረብ የመጀመሪያው እርምጃ ነው። ከልብ በመነጨ ጸሎት፣ እግዚአብሔር ልብሽን እንዲገልጥልሽ ጠይቂ። በግንኙነቱ ውስጥ ሰላምና እርካታ ይሰማሻል? ወይስ ጭንቀትና አለመረጋጋት? እግዚአብሔር የሰጠው ሰላም ምልክት ሊሆን ይችላል። ገላ. 5:22-23 ላይ እንደተገለጸው የመንፈስ ፍሬዎች (ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግስት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ ታማኝነት፣ የዋህነት፣ ራስን መግዛት) በግንኙነታችሁ ውስጥ ይገኛሉ? ይህ ሰው ወደ እግዚአብሔር እንድትቀርቢ ያበረታታሻል? መንፈሳዊ ሕይወትሽን ያሳድጋል? ወይስ በተቃራኒው? ግንኙነታችሁ በመጽሐፍ ቅዱስ መርሆዎች ላይ የተመሠረተ ነው? (ለምሳሌ፦ ሐቀኝነት፣ መከባበር፣ መስዋዕትነት) 2 ቆሮ. 6:14 "ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትተባበሩ" ይላል። ይህ ሰው ክርስቲያን ነው? እምነታችሁ አንድ ነው?
Feb 28, 2025