ሰላም ምጥጥ ንጥት ያልኩ ገፉማ መልክ የሌለኝ አጭር ፀጉሬን ከመልኬ ጋር ስታዩት የተገለበጠ መጥረጊያ ነው ሚታያቹ ነገርግን ፂም አለኝ ሰውነቴም አጭር ሆኖ ደንደን ያለ ነው ሴቶች እንዴት እንደሚሳቡብኝ አላውቅም በዘመኔ ፍቅረኛ ኖሮኝ አያውቅም ግን በጣም ብዙ ሴት ጓደኞች አሉኝ ከኔጋ ስንገናኝን በጣም ቅብጥብጥ ነው ሚሉብኝ😭 ምን የመሳሰሉ መልከኛ ናቸው እኮ ጓደኛሞች ነን በስልክ ምናምን ስናወራ it's serious ግን በአካል ስንገናኝ ህፃን ልጅ እነደነሱ አይቀብጥም እንደ መዥገር ይለጣፉብኛል ሲራመዱ እጄን አቅፈው ካልሆነ ያኮርፉሉ ሲስቁ ሰው አየኝ አላየኝ የለም ድብልቅ አርገው እየጭሁ ነው ሚስቁት እና ምንድነው ነገሩ? አውቃለሁ ደረጃዬን ለፍቅረኛ ሚያበቃ ነገር የለኝም እግሬን ቆልፌ ጆሮዬን ደፍኜ ነው ስራዬን ወጥሬ ምሰራው የነሱ የህይወት ደረጃ እና የኔ ጭራሽ ለውድድር ማይቀርብ ነው ሶስቱንም በተለያየ አጋጣሚ ነው ያወኳቸው አንዷን ባጃጅ ውስጥ አንዷን ኮሌጅ ውስጥ አንዷን ig ላይ ሁለቱ በጣም ቆንጆ የሀብታም ልጆች ናቸው ከኔጋ ጭራሽ match አያረጉም እና ምን ጉድ ነው ወገኔ? ከአንዷ ከድሮም ፍቅር ይዞኛል ግን ደሀ ሲያፈቅር አያምርበትም ብዬ ዝም አልኩ እና የኔ ጥያቄ የሶስቱም ፀባይ ለምን እኔጋ ሲመጡ ይለወጣል ለሁለቱ የኔን ጓደኞች አስተዋውቂያቸው ነበር ጭራሽ አይሆንም እና እኔጋ ብቻ ለምን? ይወዱኛል የሚል expectation የለኝም ግን ለምን እንደሆነ ማውቅ እፈልጋለሁ🙏
Jun 10, 2026እሱን ተወው እና ለምን አጫጭር ወግ መፃፍ አትጀምርም
Jun 11, 2026