ሰላም 1 ጥያቄ ነበረኝ እኔ UK ነው ምኖረው እናም አንዲት መኪና አለቺኝ እናም ሀገር ቤት ይዣት ሄጄ ለወንድሜ ልሰጠው አስብያለው ግን እንዴት እንደምወስደው አላውቅም:: እንዴት ነው መኪናውን ወደ ሀገር ቤት ይዝሄው መግባት ምችለው? አመሰግናለሁ
Jun 09, 2026መውሰድ ትችያለሽ ህጋዊ የመኪናዋ ሰነዶች ያስፈልጉሻል (ያንች ለመሆኗ) እሱን ሰነድና መኪናዋን ይዘሽ ቲልቡሪ ሄደሽ ሁለት አይነት ወላላክ ያስመርጡሻል - አንደኛው ርካሽ ነው ሁለተኛው ለኤሌክትሪክ መኪኖች የሚሆነው ውድ ነው። በኮንቴነር ነው የምትጫነው ከሁለት በአንዱ ጅቡቲ ወደብ ይወስዱልሻል ከጅቡቲ አዲስ አበባ በመኪና ትሄዳለች ከገቢዎች ክሊራንስ ካገኘሽ በሁዋላ ተመዝግባ የኢትዮጵያ ታርጋ ይሰጣና መንዳት ይችላል። ክፍያው ለቲልቡሪ መላኪያትከፍያለሽ ኢትዮጵያ ደግሞ ቀረጥ ያስከፍሉሻል። እስከ ጅቡቲ 1700 ፓውንድ እስከ አዲስ አበባ 1000 ፓውንድ ይወስዳል የቆየ ዋጋ ነው አሁን ጨምሮ ሊሆን ይችላል አንዳንዴ ከጅቡቲ በኋላ ያለው ዋጋ ከመኪናዋ ዋጋ በላይ ይሆናል የምመክርሽ መኪናዋን መሸጥ ከቻልሽ ከአዲስ አበባ ቢገዛ ፕሮሰሱንም ቀረጡንም ማረፍ ይቻላል መልካም እድል!
Jun 10, 2026