ሰላም የሁላቹንም ሀሳብ እፈልጋለሁ pls‼️ ምን መሰላቹ ስራ ወይስ ትምህርት መወሰን ስለከበደኝ ነው አሁን ላይ የጊቢ ተማሪ ነኝ ልጨርስ 2 አመት ይቀረኛል አባቴ እና እናቴ divorce ካደረጉ አመታት አለፉ እናቴ እና ታናናሾቼ በክራይ ቤት ነው ሚኖሩት ግን እናቴ ብቻዋን Afford ማድረግ እያቃታት ነው በጣም ችግር ላይ እንደሆኑ ስደውል ገና ከድምፅዋ ነው ማቀው እኔም ጊቢ በዚህ ሁኔታ መማር ትርፉ ችግር ነው ልማር ብል እንኩዋን ገና ከአሁኑ የሚያሳስበኝ መመረቂያ ፁሁፍ ስሰራ project ሲሰጥ በምን እንደምሰራ ነው እና ትምህርቱን አቁሜ ስራ ልሰራ አሰብኩ ምን ትሉኛላቹ እናቴ ብሰማ በጣም ነው ምታዝነው ግን የመጣው ይምጣ ብዬ መስራት እያሰብኩ ነው ልክ ነኝ ቢያንስ ለታናናሾቼ የሚፈልጉትን ባላደርግ የሚያስፈልጋቸውን እንደምንም ለማድረግ አስቤያለሁ ስራ ማሰራት ምፈልጉ ቀልጣፋ እና ተግባቢ ነኝ ነገሮችን በቀላሉ እለምዳለሁ ጎበዝ ተማሪ ነኝ / ነበርኩ ያው ካቆምኩት ብዬ ነው🥲 እና በናታቹ ሁላቹም ሀሳባቹን አካፍሉኝ እናንተ ብትሆኑ ትምህርቱን ትማራላቹ ወይስ አቁማቹ ወደ ስራ ህይወት ሊቀይር የሚችል ብቻ ከእጅ ወደ አፍም የሚያደርሰን ይሁን ብቻ ምን ልስራ ምን አይነት ስራ የት ልቀጠር ምታቁት🙏
Feb 25, 2025ስራ እየሰራህ ትምህርቱን የማታ መማር ትችላለህ በጣም ቢከብድም እንደ ምንም እንደዛ ለማድረግ ሞክር እና እናትህም አያዝኑም የሚያስፈልግህን ሰርተህ ለመሙላት ትሞክራለህ። በርታ😊
Feb 26, 2025