ወልድ እግዚአብሔር በሰርጉ ቤት ወይን ባላቀበት ጊዜ ድንግል ማርያምን አንቺ ብሏታል አላከበራትም ስለምን እንደዛ አላት ለሚሉ አማኞች አጭር መልስ ብትሰጡኝ
Oct 10, 2020ጌታችን በቃናዘገሊላ ድንግል ማርያምን'' አንቺ ሴት'' ሲላት አላከበራትም ብሎ ለማሰብ ከባድ ነው ም/ክ በትዕዛዛቱ ላይ እርሱ እራሱ" እናት አባትህን አክብር "ብሏልና ። እንኳን በድንግልና ለፀነሰችው፣ ወልዳ ላጠባችው፣ አቅፋ ለተሰደደችው እናቱ ቀርቶ የሰቀሉትን እንኳ በትህትና አዋርቷልና። ሌላው ደሞ በእኛ አባባል ሳይሆን በዚያን ግዜ የተለመደ የዕብራይጥ አነጋገር ስለነበር በንቀት አባባል አለ ማለት ከባድ ነው። እና ደሞ እየተናገረ ያለው አምላከ አማልክት ጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ መሆኑን ካወቅን ሲጀመር እንዴት በንቀት ተናገረ ይባላል፤
Oct 11, 2020