Selam እንዴት ዋላችሁ በ መፅሀፍ ቅዱስ ወንድ ልጅ ከአንድ በላይ ማግባቱ ልክ አለመሆኑን የሚያሳዪ ምዕራፍ ወይም ጥቅስ ብጠቁሙኝ...
Feb 18, 2025ከመነሻው ዘፍጥረት 2: 18 እግዚአብሔር አምላክም አለ፡— ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት። [የሚመቹትን አይደለም "የሚመቸውን" ] ዘፍጥረት 2: 24 ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ በሚስቱም ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። [በምስቱም አለ እንጂ በሚስቶቹም አላለም] ማቴ.19: 5 አለም፡— ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ ከሚስቱም ጋር ይተባበራል፥ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ፡ የሚለውን ቃል አላነበባችሁምን? 6 ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም። እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው። [ሁለቱም ይላል እንጂ ሶስቱ ወይ አራቱ አይልም] ኤፌ. 5: 23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና። [ባል የሚስት እንጂ "ባል የምስቶቹ" አይልም] 1ኛ ቆሮ.7: 2 ነገር ግን ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራስዋ ባል ይኑራት። [ግልፅ ነው ይሄ] ቆሮንጦስ መልዕክትን ብታነበው በግልፅ ታገኘዋለህ ::
Feb 18, 2025