selam i'm Protestant still now. ነገር ግን ስጋዬ እንጂ መንፈሴ ወደ ቅድስት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከሄደ ሰንበትበት ብሏል ነገር ግን አሁን ቀጣይ የሚመጣዉ የአብይ ፆም እስከ ዛሬ የረከሰዉን እኔነቴን ወደ ትክክለኛዉ መንገድ ለመዉሰድ ጥሩ አጋጣሚ ነዉ ብዬ አሰብኩ እናም በትብብር መልኩ ብትመልሱልኝ በጣም ደስ ይለኛል ቀጣዬቹን ጥያቄዎች 1, ኦርቶዶክስ ለመሆን ምን ምን ነገሮችን ማድረግ አለብኝ. 2, የእስከዛሬ ስራዬን ሳስበዉ በጣም ይቆጨኛል ለምሳሌ መድረክ ላይ እንፀልይልህ ትወድቃለህ ምናምን ብለዉ ህዝቡን ሲያጭበረብሩ አብሬ ተሳታፊ ነበርኩ ነገሩ ከዛም በበለጡ ነገሮች ተሳትፌአለዉ እናም ንስሀ መግባት የምችለዉ እንዴት ነዉ? 3, ኦርቶዶክስን ለመቀበል የትኛዉ መሄድ ያለብኝ ቦታዎች አሉ ? ለምሳሌ ገዳማት ምናምን... 4, ኦርቶዶክስን እንደተቀበልኩ ወዲያዉኑ የቤተክርስቲያኒቱን ትምህርት መዉሰድስ እችላለሁ ? 5, መጠመቅ ያለብኝ የትኛዉ ቤተክርስቲያን ነዉ? አመሰግናለሁ።
Feb 16, 2025እንኳንም መጣህ 1 በመጀመሪያ ንሰሀ አባት ስለሌለህ ቤተክርስቲያን ጊቢ ሄደህ ያገኘኽውን ቄስ ስጠይቅ ሁሉንም ይነግሩሀል 2 ንሰሀ እምገባው ነሰሀ አባትህ ጋር ነው 3 ቤተክርስቲያን ይሁን እንጂ የትም መቀበል ትችላለህ 4 ትችላለህ ግን ቲንሽ ብትረጋጋ ጥሩ ነው 5 የትኛውም ቤተክርስቲያን ትችላለህ
Feb 16, 2025