ጥያቄ #ለክርስቲያኖች ከእየሱስ ቡሃላ የሚመጣው ነብይ ማን ነው❓ ዘዳግም 18:18 ከወንድሞቻቸው መካከል እንደ አንተ ያለ ነብይ አስነሳላቸዋለሁ ፣ ቃሌን በአፉ አደርጋለሁ ፣ የማዝዘውን ሁሉ ይነግራቸዋል። ትንቢተ ኢሳያስ 29:12 ደግሞም መጽሐፉን ማንበብን ለማያውቅ፡— ይህን አንብብ፥ ብለው በሰጡት ጊዜ፥ እርሱ፡— ማንበብ አላውቅም ይላቸዋል። ማን ነው ማንበብ የማይችለው🤔 ነብዩ ሙሀመድ መፃፍና ማንበብ እንደማይችሉ ይሰመርበት
Feb 14, 2025ጥያቀው በመጀመሪያ ከሽፈዋል መሐመድ ወረደልኝ መጸሐፍ አለ እን ቃሉን በአፉ አልተደረገም እና የእግዚአብሔር ለሕዝቡ አላደረሰም። ሁለተኛ ከወንድሞቻቹ የተባለው እስራኤላውያን መሆን አለበት መሐመድ ደግሞ እስራኤላው አይደለም ። መልሱ ኢየሱስ ነው ይሄው👇 ሐዋርያት 3 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁹-²⁰ እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም። ²¹ እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ የተናገረው፥ ነገር ሁሉ እስከሚታደስበት ዘመን ድረስ ሰማይ ይቀበለው ዘንድ ይገባልና። ²² ሙሴም ለአባቶች፦ ጌታ አምላክ እኔን እንዳስነሣኝ ነቢይን ከወንድሞቻችሁ ያስነሣላችኋል፤ በሚነግራችሁ ሁሉ እርሱን ስሙት። ²³ ያንም ነቢይ የማትሰማው ነፍስ ሁሉ ከሕዝብ ተለይታ ትጠፋለች አለ። ²⁴ ሁለተኛም ከሳሙኤል ጀምሮ ከእርሱም በኋላ የተናገሩት ነቢያት ሁሉ ደግሞ ስለዚህ ወራት ተናገሩ። ²⁵ እናንተ የነቢያት ልጆችና እግዚአብሔር ለአብርሃም፦ በዘርህ የምድር ወገኖች ሁሉ ይባረካሉ ብሎ፥ ከአባቶቻችን ጋር ያደረገው የኪዳን ልጆች ናችሁ። ²⁶ ለእናንተ አስቀድሞ እግዚአብሔር ብላቴናውን አስነሥቶ፥ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ፥ ሰደደው።
Feb 14, 2025