Hey guys Tyakeye semonun tsomm alneber metsom jemerku metseley endihum beken wst metsaf kdus manbeb jemerku bzu ngr ale adel erasen lemekeyer eyetarku nw gn beka wste demo metfo ngerochn yasbal yne hasab adelem setan nw miyasasbegn erasen edtela metfo ngr endasb yaregegn ena atrebim tselyeshm lewt yeleshm eyalku erasen eyewekesku nw eyetelawm nw ewnet gn egziyabher ykr ylegnal arklgn yhen kfu hasab eyalku nw ebakachun tebaberugn yehone ngr belugn😭🙏🙏
Feb 14, 2025እንደ ተጨማሪ ሁሉም ነገር የሰይጣን ፈተና መሆኑን አውቀን ነቅተን ይበልጥ በጸሎት መቅረብ ነው እንደ ጥንካሬያችን መጠን የፈተናው መንገዱን ስለሚቀያይር ነው አሁን ለመንፈሳዊነት ቆርጠሽ እንደተነሳሽ ስላወቀ ከስሩ ሊጠልፍሽ እና ሊያስወድቅሽ ስለፈለገ ነው ጥርጣሬ፣ጭንቀት ምናምን እንዲሰማሽ ሚያደርገው ስለዚህ ነቅተሽ ይበልጥ ለጸሎት ቅረቢ ከፈተና መንገድ አድነኝ እንዳልሰናከል ጠብቀኝ አለማመኔን እርዳው እያልሽ ጸልዪ በእምነትሽም እንድትጠራጠሪ ሚያደርግሽ ዋናው መንገዱን ወይም መስመሩን ሊዘጋብሽ ስለፈለገ ነው የኔ ሃሳብ በእግዚአብሔር ነው እያልሽ የአንቺ ሃሳብ ያልሆነውን ግን ደሞ በውስጥሽ ሚመላለሰውን ነገሮች ተቃወሚ ስለ ጉድለት ከሆነ ሁላችንም ሊኖርብን ይችላል ይህም እንድንሞላው እንጂ እንድንሳቀቅበት አይደለም ለምሳሌ መንፈሳዊነት ሊጎለን ይችላል ስለዚህ ወደ መንፈሳዊ ነገር ገብተን ሙሉ መሆን እንጂ ዝምብለን ተቀምጠን መንፈሳዊነት ጎደለን እያልን እንድንቆጭ መሆን የለበትም ስትጸልዪ በከንቱ እንደሆነ እንዲሰማሽ የሚያደርገው ይሄም በአጭሩ ፈተና ነው እንዳንጸልይ ያደርገንና ከዛ ያ አልፈን ስንጸልይ ደሞ ዝምብለን እየለፋን እንደሆነ በከንቱ እንደሆነ እያረገ ይፈትነናል መጽሐፈ መነኮሳት ሚባል የቤተክርስቲያን መጽሐፍ አለ እና ከጸሎት ጀምሮ የሰይጣን ፈተናዎች እና እንዴት እንዳለፉት የሚናገር መጽሐፍ ነው ማንበብ ትችያለሽ ከፈለክሽ ወይም የሰይጣን ውጊያዎች የሚል ታዋቂ የአቡነ ሺኖዳ መጽሐፍ አለ እሱን አንብቢ አንዳንዴ የሆነ ነገር ያስጨንቀናል ይደብረናል ይከፋናል ለምን እንደሆነ ምክንያቱን እንኳን አናውቀውም እና ምክንያቱን እንኳን እንዳናውቅ አርጎ ነው ሚፈትነን እንደዚህ ሲያጋጥም በቃ ፈተና መሆኑን አውቀሽ አባታችን ሆይ ብለሽ 3ጊዜ ስገጂ ደጋግመሽም አማትቢ በመጨረሻም ትልቁ ነገር ከንስሐ አባትሽ ጋር Communicate አርገሽ ንስሐ ግቢ ለቅዱስ ቁርባንም ቅረቢ በየመሃሉ ሚገጥሙሽን ችግሮች ምናምን ከንስሐ አባትሽ ጋር እየተመካከርሽ ታልፊዋለሽ አያሳስብም
Feb 14, 2025