ሰላም ቤተሰብ አዲሱ የ ዲ/ን አቤል መክብብ የመዝሙር አልበም የማገኝበት ቻናል ጠቁሙኝ። አመሰግናለሁ።
Feb 10, 2025የአቤል አዲሱን የመዝሙር አልበም ኖት እየያዝሁ በጥልቀት ሰማሁለት። 13ቱም መዝሙሮች ግጥሞቻቸውም የሙዚቃ መሳሪያዎቹም እንከን አልባ መዝሙሮች ናቸው። ያው አልበሙ 16 መዝሙሮችን የያዘ ቢሆንም ሶስቱ እንክርዳድ መዝሙሮች ስለሆኑ ዝምብለን እናልፋቸዋለን። የሆነ ቀን ተለቅሞ ይወጣሉ በሚል ጥልቅ ምኞት😁 ደረጃ ለማውጣት ቢያስቸግሩም በጥበብ እንደምንም ለይቼ በጣም ተደጋግሞ መሰማት ያለባቸው ሰባቱን መዝሙር ምረጥ ከተባልሁ…. 15ኛ ትራክ እንዳላጠፋ ሰው፣ 11ኛ ትራክ በማይነገር ስጦታ፣ 8ኛ ትራክ እንግዲህ ምን ልበል፣ 9ኛ ትራክ በማለዳ፣ 5ኛ ትራክ መሸሸጋዬ ነው፣ 1ኛ ትራክ ተመስገን፣ 16ኛ ትራክ ይተካል እግዚአብሄር የሚሉት ትራኮች ከፍ ተደርጎ የተሰቀሉ መዝሙራት ናቸው! ከመዝሙሩ አልበም አንዱን መዝሙር ብቻ የአልበሙን ውበት ለማሳየት ትንሽ ሰፋ አድርጌ አሳቡን ለማሳየት ልሞክር። ከላይ እንዳልኳችሁ ጥልቅ የሆነ መዝሙር መስማት ልምድ ላለው ሰው በነጠላ መዝሙሮቹ ራሱ ሰፋ ያለ ኮመንተሪ መጸሃፍ የሚቻል መዝሙሮች ናቸው መዝሙሩ የሚገኝበት የአልበሙ ቁጥር: 16ኛ (የመጨረሻው የአልበሙ መዝሙር)። ርእሱ: ይተካል እግዚአብሄር አገልጋይ ለቤቱ። የመዝሙሩ ጠቅላላ አሳብና ይዘት: በዘመናት ታማኝነቱ የማይነጥፍበት እግዚአብሄር አገልጋዮችን በቤቱ ይሾማል። በጉልበታቸው ያልዛሉ፣ ብርቱ የሆኑ አገልጋዮችን ጸጋውን እያካፈለ በማይሰስት ቸርነቱ ለቤቱ አገልጋዮችን ይሾማል። ጸጋው ደግሞ ከትላንት ዛሬ፤ ከዛሬ ለነገ እየበዛ ብርቱ አገልጋዮችን ለቤቱ እያበቃ እየበዛ የሚሄድ ነው። ዘማሪውም ይህን ቅድመ ልባዌ መረዳት በመያዝ እውነትነቱን ለማስረዳት ወደ ቃሉ ይወስደናል። ሙሴ ህዝበ እግዚአብሄርን የመራበት የ40 አመቱ ጥበብ፣ ማስተዋልና በረከት ከሙሴ ጋር ወደ መቃብር አልወረደም። ይልቁን በረከቱ፣ ጥበቡ፣ ማስተዋሉና ሞገሱ በዝቶ ወደ ብላቴናው ኢያሱ ተሻገረ እንጂ። መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው የእስራኤል ንጉስ ኢያሱን ከሌሎች አገልጋዮች ይልቅ በመምረጥ በፊቱ በጸጋው እንዳቆመ ዘማሪው የአገልጋዮችን መተካካት እያሰበ ይዘምራል። ዘማሪው ከህዝበ እስራኤል የስልጣን ተዋረድ ተሻግሮ በዘመነ ነቢያት የተከናወነውን ሌላ መተካካት በመጸሃፍ ቅዱስ የነቢዩ ኤሊያስና ኤልሳን ታሪክ እያነሳ በዜማ ያዜማል። ኤሊያስ በእሳት ሰረገላ ወደ ላይ ሲወሰድ የጸጋውን ማስተላለፊያ መጎናጸፊያውን ይዞ አልወጣም። ይልቁን ህዝበ እስራኤልን በነቢይነት ለሚያገለግል ለደቀ መዝሙሩ ለኤልሳ ተወለት እንጂ። ኤልሳም ፍጹም እጥፍ ድርብ በሚሆነው በአምላኩ ጸጋ አገለገለ። የጸጋውን ሰጪ እየረሱ የተቀበሉትንም ጸጋ እያኮሰሱ በራሳቸው የቤቱ አገልግሎት በጥረታቸው እንደተገኘ ለሚቆጥሩ አገልጋዮች እንዲህ እያለ ያሳስባቸዋል። ከኔ ብቻ በቀር ማነው ያለው ሌላ፣ ስሙን አገልግሎ ዝናሩ ያልላላ። እንዲህ አትበሉ እግዚአብሄር ዘገየ፣ ይሾማል ለቤቱ ጠላት አይኑ እያየ በዚህ ውስጥ ዘማሪው የራሳቸውን ፐርሰናል ከልት ለመፍጠር ለሚሞክሩ ለቤቱ አገልጋዮች ማሳሰቢያ ጣእም ባለው ዜማው ያሳስባል። አገልግሎት ሁሌ የጸጋ ውጤት መሆኑን ለሚረሱ አገልጋዮች ጥሩ ምክር ነው! ሿሚውም ጸጋ ሰጪውም እግዚአብሄር ነው። ተሿሚው ለቤቱ የሚሰራ የቤቱ ባላደራ ነው። ብንቀድስ፣ ብንዘምር፣ ወንጌልን ለማያምኑ ሰዎች ብንመሰክር ወደ ሰማይ ቤት መሄዳችን አይቀርም። ታማኙ እግዚአብሄር ለቤቱ ደግሞ እንደገና ሌሎች አገልጋዮችን ያስነሳል። አገልጋዮቹ ደግሞ ከቀደሙት አገልጋዮች በበለጠ ዘመኑን መዋጀት የሚችሉ፣ በጸጋ የበረቱ፣ እጅግ የጸኑ እንደሆኑ ዘማሪው በውብ ዜማው ያስታውሰናል። ለአቤላ ሸልፈኛው በዚህ አልበሙ እንደወደደው ንገሩልኝ። ሰርጎ የገቡ ሁለት ከግማሽ የሚሆኑ መዝሙሮችን ደግሞ በቀጣዩ አልበሙ እንዲያርማቸው። በርግጥ ከ16 መዝሙሮች 13ቱን ቃሉን ያማከለ መዝሙር እዛ ቤት መዘመር ትልቅ ስኬት ነው! እግዚአብሄር ጸጋውን አብዝቶ ያድልልን አቤላችን። ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን! https://t.me/christiangoodbooks
Feb 11, 2025