ሠላም እንዴት ናቹህ። ዛሬ አንድ ምክር ልጠይቃችሁ ነው። የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነኝ እና ሳላስበው ከማልጠብቃት ልጅ ፍቅር ያዘኝ። ከልጅቷ ጋር አንድ የሚያገናኘን ጉዳይ አለ እና ተገናኝተን እናወራለን። ደውየም በቴክስትም አወራታለሁ። እና ምን ችግር አለው ካላቹህ ደግሞ ልጅቷ ዘንድሮ GC ናት እኔ ከእሷ አንድ አንሳለው። ሲቀጥል ከሷ ጋር የምናወራው ስለሚያገናኘን ጉዳይ ብቻ ነው። የበፊቱን ግንኙነታችንን ሰብሬ ወደ አዲስ relationship መውሰድ ከበደኝ ምክንያቱም የእሷ ምላሽ ምን ሊሆን እንደሚችል አላውቅም። በተወሰነ ደረጃ ቀይሬ ለማውራት ሞክሬ ነበር ግን ማስቀጠሉ ከበደኝ። በአካል አጊንቼ ሳወራት free ሁናነው የምታወራኝ። በቴክስት ሲሆን ብዙ ቆይታ ነው የምትመልሰው። ትንሽ ወግ አጥባቂ ነገር ናት እሱን ነገሯንም በጣም ነው የምወደው ግን ምን ላርግ ቀርቤ ባጣትስ የሚል ፍራቻ አደረብኝ። አሁን የቀራት ደግሞ ትንሽ ጊዜ ነው ስለዚህ ምን ትመክሩኛላችሁ???
Feb 06, 2025ሞክረህ ብታጣት አይቆጭህም ወንድሜ እንዳይቆጭህ እሺ ካለች እሰዮ እምቢ ካለች አለች ነው ሞክር👍
Feb 06, 2025