የዮሐንስ ወንጌል 8
1 ኢየሱስ ግን ወደ ደብረ ዘይት ሄደ።
2 ማለዳም ደግሞ ወደ መቅደስ ደረሰ ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ መጡ። ተቀምጦም ያስተምራቸው ነበር።
3 ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዘችን ሴት ወደ እርሱ አመጡ በመካከልም እርሱዋን አቁመው፡—
4 መምህር ሆይ፥ ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች።
5 ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ? አሉት።
6 የሚከሱበትንም እንዲያገኙ ሊፈትኑት ይህን አሉ። ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ፤
7 መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ፡— ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት፡ አላቸው።
8 ደግሞም ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ።
9 እነርሱም ይህን ሲሰሙ ሕሊናቸው ወቀሳቸውና ከሽማግሌዎች ጀምረው እስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች።
10 ኢየሱስም ቀና ብሎ ከሴቲቱ በቀር ማንንም ባላየ ጊዜ፡— አንቺ ሴት፥ እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን? አላት።
11 እርስዋም፡— ጌታ ሆይ፥ አንድ ስንኳ አለች። ኢየሱስም፡— እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ፡ አላት።
12 ደግሞም ኢየሱስ፡— እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው።
echi set be dngay miyaswegr hatyat serta just like You ks beks hona neber neger gen he forgave her, ykr ymaybal hatyat yelem, yesew lej gen ke hatyat kes lemewtat tsadik mehon yasfelgewal metsdekyaw menged demo Eyesus new, esun tekebel, adis ftret tehonaleh, yedro tarikh yalfal, bedro maneneteh hlinah aykesehem
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5
17 ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።
Feb 04, 2025