ከልጅቷ ጋር አንድ ሰፈር ነን እና በቅርብ ነ የገቡት maximum 1 አመት ቢሞላቸው ነው ያን ያህልም ቅርበት የለንም ግን እኔ በፍቅሯ ልሞት ነው አይኗን ሳየው ገና እደናበራለሁ ለሰላምታ እንኳን አንገቴን ደፍቼ ነው የማልፋት.... አንድ አንዴ ደግሞ ዝም ብዬ አያታለሁ ሁሉ ነገሯ ደስ ይለኛል ፈገግታዋማ በኪዳነምህረት እኔንጃ በቃል የማልገልፀው ነው በዛ ላይ "ቆንጆ ሴት ሳይሆን ለልጅህ ጥሩ እናት አግባ" የተባለላት አይነት ልጅ ናት ስለእሷ ሲወራ የሚሰማኝ ደስታ ወደር የለውም ግን እንኳን በዛ ስታፍ ለእግዜር ሰላምታ እንኳን እፈራታለሁ በተለይ አይኗ የሆነ ነገር አለው ምን ላድርግ... ስልኳ አለኝ ግን በtext አውርቻት ነገ እንዴት ነው በበራቸው የማልፈው
Feb 03, 2025This is so cute😂 we need part 2
Feb 03, 2025