እባካቹ ከዚ በፊት ትርፍ አንጀት የተሰራላቹ ሰዎች እርዱኝ እኔ ህመሙ ከጀመረኝ 1 ወር የሆነኛል በዚ ሳምንት በጣም ነው የባሰብኝ ትርፍ አንጀት ለመሆኑ ሁሉም ምልክቶች እኔጋ አሉ እና ምን መሰላቹ ብቻየን ነው የምኖረው ቤተሰቦቼ እሩቅ ናቸው ጓደኛም ይለኝም ይሄን ነገር ብቻየን የምወጣው ይመስላቹሀል ከህመሙ በላይ ያስጨነቀኝ ይሄ ነው ቤተሰቦቼ በጣም ይጨነቁብኛል በዛ ላይ ምንም እረድቻቸው አላውቅም 😢 በየትኛው ሞራሌ ነው ኑና አስታሙኝ የምላቸው 😭 እባካቹ ብቻየን የምወጣው ከሆነ አንዳንድ ነገሮችን በሉኝ እግዚአብሔር ያክብራቹ🙏🙏
Feb 03, 2025ሐቢቢ ትርፍ አንጀት በዚህ ጊዜ ልክ አያቆይህም። ቢበዛ ሳምንት ከከፍተኛ ህመም ጋር ብትቆይ ነው። ከዚያ ካለፈ ይፈነዳና ሌሎች የሰውነት ክፍልህን ኢንፌክት ያደርጋል። ምልክቶች ሊመሳሰሉ ይችላሉ። ግን የየትኛው በሽታ ነው የሚለውን ለማወቅ መመርመር አለብህ። ቡአ ሊሆን ይችላል፣ የሆድ ድርቀትም፣ ካንሰርም... የማናውቀውንም ሊሆን ይችላል (አያድርግብህ)። 'እንዲህ ታምሜያለሁ' ከማለትህ በፊት ብትታየው መልካም ነው። ህመምህ የከፋ ነገር ወይም ቀላል ነገር ሊሆን ይችላል። መዳኑን እመኝልሃለሁ።
Feb 03, 2025