ሰለም ሰዎች እኔ M ከህይወተ ደስታ ርቋል ብዙ ፈታናዎች ደርሰዉብኛል ተስፋ በመቁረጥ ዉስጥ ነዉ የሚኖረዉ ከዚህ ህይወት እንደት መዉጣት እችላለሁ በናታችሁ ምከሩኝ
Feb 02, 2025ያለህበት መስመር የሰው ልጅ የተባለ ሁሉ የሚያልፍበት መስመር ነው። መጀመሪያ ብቻህን እንዳልሆንክ መረዳት አለብህ። ቀጥሎ ሁሉም ከየራሱ ችግር ጋር ሆኖ ነው ጥርሱን እያሳየህ ያለው። ያለ እንከን የሚኖር የለም። ደስታ፣ ሀዘን፣ ማግኘት፣ ማጣት... በህይወታችን ቢያንስ አንዴ ቢበዛ ሁል ጊዜ የሚገጥሙን ሁነቶች ናቸው። አንተ ጋር ያለው ድክመት ችግርህ ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ ችግርህን ማስወገድ/ተላምዶ መኖር አለመቻልና በልብህ ተስፋ መቁረጥን መጸነስ ነው። ህይወት ደግሞ በዚህ መልኩ ሊቀጥል አይገባም። ህይወት እንደ ጌም ነች። በየደረጃው ፈተና ይጠብቀናል። ጌሙን በእልህ አሸናፊ ሆነን እንደምንጨርሰው የህይወትንም ፈተና በትግል፣ በእልህና አስተዋይነት በተሞላበት መልኩ ልንወጣው ይገባል። ብንፎርሽ ሳንወድቅ ለመጨረስ ደግመን ጌሙን እንደምንጀምረው በህይወትም ይሳኩልናል ብለን ያሰብናቸው ሁነቶች ቢበላሹብን እንደ አዲስ መጀመር አለብን። ማድረግ ያለብህ ለራስህ ጊዜ ስጥ እና ችግሮችህን ሁሉ በቁጥር ዘርዝረህ ጻፍ። ከዚያ በሌላ ገጽ ለችግሮቹ መፍትሔ ያላቸውና የሌላቸውን ለይተህ አስቀምጥ። መፍትሔ የሌለውን አምነህ ተቀበል። ፈጣሪህ እንዲያስወግድልህ ለምነው። መፍትሔ ያለውን ደግሞ ተራ በተራ ለመቅረፍ roadmap ቅረጽ እና ወደ ተግባር ግባ። ሁሉንም በአንዴ ማስወገድ አትችልም። ስለዚህ አንድ በአንድ ለመቅረፍ ሞክር። ይቀርበኛል የምትለው ሰው ካለ አማክረው። የሰው ልጅ ሁሌም ችግር መስማት አይፈልግምና ወደ ፈጣሪህ እጅህን ማንሳቱ ደግሞ የተሻለ ነው። ያልፋሉ ብለን ያላሰብናቸው ቀናት ሁሉ ያልፋሉ። አብሽር! ቢከፋህ፣ ቢቸግርህ በገንዘብ ባልረዳህ እንኳ በሐሳብና በማጽናናቱ አብሬህ ነኝ።
Feb 03, 2025