Guys አረ መላ በሉኝ ተሰቃየሁ በቃ ምን ልበላቹ ከሰዎች ጋ መግባባት አቃተኝ።በተለይ ብዙ ሰው ተሰብስቦ ካየሁኝ ቀና ብዬ ማየት አልችልም ይጨንቀኛል፤ራሴን ያመኛል እንዲሁም ያስፈሩኛል በቃ፤ በጣም ሲበዛ ዐይነአፋር ነኝ።ሴቶችንም ቀርቤ አላውቅም፣ ምን እንደሆነ አይገባኝም ግን በጥላቻ አይን የሚመለከቱኝ እየመሰለኝ ተቸገርኩ።ይሄ ነገር ከልጅነቴ ጀምሮ ነበር የያዘኝ፤አስተዳደጌም በጣም በብቸኝነት እና በድህነት ነበር ያደኩት።ሰዎች እናቴን ጨምሮ አይነጥላ ነው ይላሉ።ነገሩ አልገባኝም በብቸኝነት ተሰቃየው።አይምሮዬ አንተ መልክ የለህም አስቀያሚ ነህ፣ሴቶቹም አይወዱህም ይለኛል።እንቅልፍ አጣሁ እና ይሄ ነገር አይነጥላ ከሆነ እንዴት አባቴ አድርጌ ነው ከዚህ ነገር ነፃ የምወጣው ?...ህይወቴ እያየሁት ተበላሸብኝ graduate ካረግኩ ይሄው 5 አመት ደፈንኩኝ፤ስራ ያጣሁት ከሰው ጋራ አለመግባባቴ ነው።በቃ በህይወት ያለ የሞተ ሰው ቢኖር እኔ ነኝ።እና የሆነ መፍትሄ ካለ አትለፉት በናታቹ በተለይ በዚ ነገር ያለፋቹ ካላቹ የሆነ ነገር በሉኝ😕😢
Feb 02, 2025ራስህን እንደዚ አሳንሰህ አትይ ካንተ የባሰ ተሰጥኦ እና መልክ ያላቸው ሰዎች ታዋቂ ሲሆኑና ጥሩ ቦታ ሲደርሱ ያየህ ይመስለኛል የምትኖረው አንዴ ነውና ደፋር መሆን አለብህ ይቺ ዓለም ለወንድ ልጅ ጦር ሜዳ ነች
Feb 02, 2025