ለምንድነው ኢትዮጵያ ውስጥ ለቅሶ ላይ ሰዎች የሚያስመስሉት? የሰውየው አስክሬን መሬት ሊገባ ሲል እኔም አብሬ ልግባ ማለት??? የሞቱ ዘመዶቻቸውን ስም እየጠሩ እየመጣ ነው ተቀበሉት ምናምን?? ቢቻል በሕይወት እያሉ የተቻለውን ሁሉ ማድረግ ከዛ ግን ሰልስት፣40, 50, 60,70 ,80 ከዛ ደግሞ ሙት አመት ምን ያረጋል? ዝክር? ምኑ ነው ሚዘከረው? የለቅሶ ባህላችን መቀየር አለበት✊! አይመስላችሁም?
Jan 30, 2025አይመስለንም።ባህሉ ምን አረገህ።ዝም ብለህ በማይመስል ነገር አቃቂር አታውጣ።መቀየር ካለበት ሰዉ ነው።40,80 ሙት አመት የሚዘከርበት ደሞ የራሱ የሆነ ትርጉም ያለው ልዩ ሐይማኖታዊ ስርአት ነው። ሲቀጥል አብሬ ልግባ እየመጣ ነው ተቀበሉት የሚል ነገር አለ?? ወይኔ mom ድረሺልኝ 😂😂 በተረፈ የለቅሶ ባህላችን መቀየር የለበትም በጣም ያረሳሳል ለምሳሌ ካርታ የሚጫወቱት ነገር ምናምን በጣም ነው የሚመቸኝ
Jan 30, 2025