ሰላም ቤተሰብ በህልሜ ጥርሴን ተነቅዬ አርቴፊሻል ሲተከልልኝ ነው ያየሁት እና I'm curious የሚያውቅ ሰው ካለ ፍቺውን ቢነግረኝ... Thanx in advance
Jan 29, 2025ስለህልሙ የምልህ ነገር አይኖርም። ነገር ግን ህልሙን ከማየትህ በፊት በነበሩት ቅርብ ቀናት ስለጥርስ አስበህ ነበር? ወይም በጥርስህ ላይ የተፈጠረ ነገር ነበር? እንደ ብሬስ ያሉ ከጥርስ ጋር የሚገናኙ ነገሮችን አስበህ/ ተከስቶ ነበር? መልስህ 'አው' ከሆነ ህልምህ የቀን ውሎህን ከማስተጋባት ውጭ ትርጉም የሌለው ህልም ነው። ራስህን አታጨናንቅበት። ስለዚህ ነገር ባላሰብክበት ወይም ባልተፈጠረበት ሁኔታ ያየኀው ከሆነ ትርጉም ይኖረዋል። በአንክሮ እንድታውቅ የምፈልገው ነገር ቢኖር ከጥርስ ጋር የተገናኘ ህልም ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ነው። ለተራ ሰውም ተናግረህ ማስፈታት የለብህም። እንደ አጠቃላይ ህልም በእንዲህ አይነት ቦታ ፍቱልኝ ተብሎ አይነገርም። ህልም ሀብት/ጸጋ ነው፤ ጸጋ ደግሞ ለሁሉ አይገለጥም!
Jan 29, 2025