ብሉይ ኪዳን ላይ የተጻፈ ትዕዛዝ ነው የስጋ ህግ ስለሆነ የእስራኤል ልጆች በስጋ ንጹህ ሊሆኑ ያስፈልግ ስለነበር ነው . . . ህጉ ስለ ስጋቸው የወጣ ነው በሀዲስ ኪዳን ግን ቃል ስጋ ሆኗል እራሱን የሰው ልጅ እያለ ተወዳጁ ህግን ሁሉ ፈጽሞታል. . . ስጋ ምንም ጥቅም የለውም ብሎ የምንድንበትን፤ የዘለዓለም ሕይወት የምናገኝበትን የነፍስ የመንፈስ ሕግ እና ስርዓት ሰርቶልን ሄዷል. . . በአሁኑ ኪዳን የተጠመቀ በእግዚአብሔር ልጅ ያመነ በሕይወቱም ቃሉን የኖረው በጽድቅ ስራ የተመላለሰ የሰው ልጅ የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ መኖር ይችላል ከላይ የተጻፉት ሕጎች ለእስራኤል ዘስጋ የተሰጠ እንጂ በእስራኤል ዘነፍስ አይሰራም. . .
Jan 27, 2025