ኢትዮጵያ ወስጥ animal violence ወይም እንስሳትን መጉዳት በጣም የተለመደ የሆነው ለምንድነው? ሰዎች ምንም ያላረጋቸው ዉሻ ላይ ለምንድነው ድንጋይ የሚወረውሩት? በነገራችን ላይ ሰዎች እንስሳትን treat የሚያደርጉበት መንገድ አይምሮዋቸው ምን ያህል ተለውጧል የሚለውን ያሳያል። አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ሄዶ ለመኖር የሚመኝባቸው ሀገራት እንስሳትን የሚንከባከቡበት መንገድ የሚደንቅ ነው። ከሁሉም የሚገርመው በእግዚአብሔር የምታምኑ ሰዎች እንዴት እንስሳት ላይ ትጨክናላቹ? በዙ ግዜ ደግሞ ለእንስሳት ከፉ የሆኑ ሰዎችን አስተውላችሁ ከሆነ ልባቸው በጣም ክፉ ነው። የእንስሳት የስቃይ ድምፅ ምንም የማይመስላቸው ሰዎች ሰዉንም ለመጉዳት ምንም አይመስላቸውም። ከህፃናት ንፁህ ልብ መማር የምንችለው ነገር አንዱ እንስሳትን መውደድ ነው። እናንተ ምን ታስባላችሁ?
Jan 23, 2025ጥቂት ህፃናት እና ግለሰቦች ስለሚያደርጉት ነገር ኢትዮጵያ ብሎ ማውራት አላማው አይዋጥም.. ሲቀጥል ሌላው አለም ያልከው ውሻን አይደለም የሰው ብልትን በትላልቅ ሬስቶራንት ሚመገቡ ናቸው .. እንደውም እንደኢትዮጵያዊ ውሻ ወዳድ አይቼ አላውቅም ግን በልክ ነው እንደተቀናጡት ካላጠባሁ ካላለበስኩ ጥፍሩን ካልቆረጥኩ እያሉ እንደሚላጡት እንኳን ለእንስሳ ለሰዎችም አልታደልንም::
Jan 23, 2025