ሠላም እያደጋቹ ስትመጡ ሁሉም ነገር እየጨለመባቹ ነው ልክ እንደኔ? ነገሮችስ ሳይገባቹ ፈገግ ብላቹ ታውቃላቹ?ወጣትነት የሚሉት ትርጉም ያጣ ምስቅልቅል ያለ ህይወት የመኖርን ጣዕም እያጠፋባቹ ነው ልክ እንደኔ?ይህ ስሜት እኔጋ ብቻ ነው ያለው ወይስ ሌሎቻቹም ጋነው?ይሄን ህይወት ያለፋቹ ደሞ ምከር ስጡ በተለይ ከ30 በላይ የሆናቹ
Jan 21, 2025እየጨለመብን የመሰለን እውቀቶች ከሚታሰበው በላይ በጣም ሰፊ እንደሆኑና ይህን ሁሉ ማወቅ እንደማንችል ስናስብ ነው። ሁሉን ነካክተን መጨረስ እንደማንችል ካወቅን እንዴት አይጭነቀን? ለዚህ መፍትሔው የምትወደው/ስትሰራው ብቃትህ የሚታይበትን አንድ እና ሁለት እውቀቶችን/ስራዎችን ማስተር አድርጋቸው። ከዚያ በኋላ ኅብረተሰቡ አዋቂ ነህ ብሎ ባትማር እንኳ የዶክትሬት ማዕረግ ሲያሸክምህ ታየዋለህ። ቲዲ አፍሮ ሳይማር ዶክተር ለመባሉ በቂ ምሳሌ ነው። የትኛው ቪድዮ ላይ እንደሰማሁት ባላስታውስም በግርድፉ እንዲህ ይላል፦ "ይህች ምድር ሁሉን አውቃለሁ የሚለውን አትሸልምም። ይልቁንም አንድ እውቀት ይዞ በዚያ እውቀት ጥልቅ የሆነ መረዳት ያለውን ትሸልማለች።" ይላል። የሚሰራ አይጨነቅም/አይጨልምበትም። መስራት እየቻልን ባለመስራታችን የጎደለብን ነገር ሲኖር ነው የሚጨንቀን። ለራስህ በቂ ጊዜ ስጥ እና የሚያስጨንቅህን ነገር ጻፍ። መንስኤው ምን እንደሆነ አስከትለህ ጻፍ። መፍታት የምትችለውን ችግር ጻፍ። የምትወስደውን action ጻፍ። ወደ አክሽኑ ግባ። መፍታት የማትችለውን ችግር ጻፍ። መፍታት ካልቻልከው መጨናነቅህ መፍትሔ መሆን እንደማይችል አምነህ አቅም እስኪሰጥህ ለፈጣሪህ ተወው። ይህን ምክር ለመስጠት ከ30 በላይ መሆን አይጠበቅም። ወጣትነት የማይመለስ ስጦታ መሆኑን የተረዳ አስራዎቹ እና ሃያዎቹ ቤት ያለ ወጣት፣ ያመለጠው አርባዎቹ እና ሰባዎቹ ቤት ያለ ጎልማሳ ሽማግሌ ሊመክር ይችላል።
Jan 22, 2025