Selam guys ke bf gar ketetalan 5 amet alfonal esun yene endihon bemimegnibet ena betegodawibet gize zor bilo enkua alayegnim neber gin ahun ke sibirate agegemku ena selamawi destegna hiwetin menorin jemerku balkubet seat exe liyarfilign alchalem digami abren enihun alegn ene gin erasen megenbat new enji wend ayasfeligegnim biye embi alkut ena beteleyaye silk eyedewele yizitibignal ene uv new yalewit ena betam yisedbegnal hule silk block adergalew gin yemidewilibet or text yemiyadergibet silk ayatam. Silken endalkeyir degmo betam yasfeligegnal ,ena ehit wendimoch kezi befitim break up badereku gize yenante qena mikir agizognal ena leza ameseginalew ,besu mikniyat le bealim hone le ereft wedebet megbat alchalkum ...betam ferichalew ,yemigodagn new yemimeslegn ena endet litenkek 🙏🥺
Jan 20, 2025መጀመሪያ መንከባከቡ የርሱ ግዴታ ነበር። የናቀው ንብረት ውድ መሆኑን ካወቀ በኋላ በግድ ላግኘው ቢል ምን ዋጋ አለው? አለፈ። በእምቢታሽ ጽኚ። ከላይ እንደተጻፈልሽ መረጃዎችን በሚገባ አስቀምጪ። የቅርብ ጊዜውን ኢንሲደንት የረሳሽው አይመስለኝም። ያለችበት ጊቢ ሄዶ ወደድኳት ያላትን ሴት የገደለውን ወጣት ሰው ታሪክ ማለቴ ነው። ካለሽበት ጊቢ መውጣት አቁሚ። ለጊዜውም ቢሆን ሲም ካርድሽን ዝጊና አዲስ ሲም ተጠቀሚ። ቤተሰቦችሽ ሊፈልጉሽ ስለሚችሉ ሲም መቀየርሽን ሳታሳውቂ ምክንያት ፍጠሪ። ለምሳሌ "ጥናቴ ላይ መበርታት ስለፈለግኩ ቀን ቀን/ ማታ ማታ ስልኬ ዝግ ስለሚሆን አትጨነቁ። ስትፈልጉኝ ጓደኛዬ ከኔ ጋር ስለምትውል በጓደኛዬ ስልክ ደውላችሁ ልታገኙኝ ትችላላችሁ።" ብለሽ አዲሱን ቁጥርሽን ስጫቸው። አንድ ይቀርበኛል ለምትዪው ቤተሰብ ይህን ጉዳይሽን አሳውቂ። ወንድ ቢሆን የተሻለ ነው። የዚህን ጀዝባ ወላጆችን የምታውቂ ከሆነ ወይም ደግሞ አንድ ጊዜ ጨክነሽ ቤተሰቦቹ ጋር ሄደሽ የልጃቸውን ስራ ከነማስረጃዎችሽ አሳውቂያቸው። ልጃቸውን እንዲያሳርፉ እና ለህይወትሽ ስጋት እንደሆነ ንገሪያቸው። ለወላጆቹም ይህን ስትነግሪ ሪከርድ ማድረግሽን አትርሺ። መረጃዎችሽን በሙሉ ለኔ ቅርብ ነው ለምትዪው ሰው በየጊዜው እየላክሽለት Update አድርጊ። አትፍሪው! ይህ ማለት ግን አትጠንቀቂ ማለት አይደለም። መጠንቀቂያዎችሽን ሁሉ ይዘሽ ነው አለመፍራት። የመጨረሻ የማይሳካ ከሆነ ለወላጆችሽ አሳውቂ። የሞከርሻቸውን አማራጮች ሁሉ ንገሪያቸው። መረጃዎችሽን አሳዪ። እነርሱ ለልጃቸው እንዴት መከላከል እንዳለባቸው ያውቃሉ። ልኩን ያስገቡታል።
Jan 21, 2025