Mejemerya enkuan aderesachu🤗🤗🤗 Letmket eski yalachun twsta agarun, fegeg miyasblm miyastemrm kale ensma😊 Shukren🤗 melkam beal🤗
Jan 19, 2025የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነበርኩ እና በግቢ ጉባኤ ነበር የምናከብረው.... ወደ ገጠር ያሉ እና ምእመናን ጥቂት የሆኑባቸው 2 ቤት ክርስቲያኖች አቡነ ሀራ ድንግል እና አቡነ ሀብተ-ማርያም እና አባላት ለሁለት እንከፈል እና የከተራ ለት ተሰብስበን እየዘመርን እንሄዳለን እና የሚገርመኝ እኛ እስክንሄድ ድረስ ምንም ፕሮግራም አይጀመርም ይጠብቁናል እና ስንደርስ ከእኛ ውስጥ ያሉ ዲያቆናት ፕሮግራሙን ይመራሉ ያስተባብራሉ እየዘመርን አጅበን ወደማደሪያው እንሄዳለን እዛው ድንኳን ጥለን እየዘመርን እና አንዳንዶችም በአገልግሎት እናድራለን የጥምቀት ቀን ጠዋት አስቀድሰን ፀበል ተጠምቀን እየዘመርን ወደ ቤቱ አስገብተን በቤተ ክርስቲያኑ የተዘጋጀውን በረከት ቀማምሰን ወደ ግቢያትን እንመለሳለን ....ብዙ አስለፈለፍሽኝ ብቻ በጣም ደስ ይል ነበር
Jan 19, 2025