ኢየሱስ ለእናንተ ማነው? (Answer based on your own encounter and don't be limited by your religion/teachings)
Jan 18, 2025ኢየሱስ ይወደናል፤ እኛም እንወደዋለን። በርሱ ያላመነ እምነቱ ጎደሎ ነው! እናቱ.. እናቱ ምድራችን ላይ ካሉ ሴቶች ሁሉ የላቀች፤ ለንጽህናዋ ከፈጣሪዋ በላይ ምስክር የማያሻት፣ ትሁት የነበረች፣ ንጹህ ሆና በምድራችን ካለው የስነ-ተዋልዶ ስርዓት ልዩ በሆነ መንገድ በፈጣሪዋ እገዛ ክቡሩን ሰው የሆነውን ኢየሱስን ወለደች። ሲያድግና ካደገ በኋላ ከተመረጡ የአምላክ ሰዎች በቀር ተራ ሰው ሊያሳየው የማይችለውን ታላላቅ ተዓምራት የሰራ፣ አሁንም በህይወት ያለ፣ ወደፊትም የሚመጣና ምድራችንን ከኢ-ፍትሐዊ ስርዓት ነጻ የሚያወጣ.. ኋላም በላኪው ፈቃድ መራራዋን ሞትን የሚጎነጭ ታላቅ ሰው ነው። የአላህ ሰላትና ሰላም በርሱም በእናቱም ላይ ይሁን። ለኛ ለሙስሊሞች ኢየሱስ/ዒሳ ይህ ነው።
Jan 18, 2025