የህግ እውቀት ያላችሁ አግዙኝ እኪ አንድን ድርጅት (PLC) ከስሼ ወደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አቀረብኩት። መልሱ ላይ: የመጀመርያ ደረጃ መቃወሚያ 1) ይህ ክርክር በከሳሽ ግለሰብና በተከሳሽ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መካከል የሚደረግ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ስለሆነም በአዋጅ ቁጥር 1234/13 አንቀፅ 5(ደ) መሰረት ይህ ፍ/ቤት በግለሰቦች መካከል የሚኖርን የገንዘብና የውል ጉዳይ ከሚመለከት በስተቀር በግለሰብና በንግድ ሕጉ መሰረት በሚተዳደሩ ማህበራት መካከል የሚኖርን ክርክር ተቀብሎ የመዳኘት ስልጣን የለውም፡፡ ይህ ፍ/ቤት መጥሪያውን በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 233 መሰረት ለተከሳሽ ከመላኩ በፊት በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 231 መሰረት የስረነገር ስልጣን እንዳለው አጣርቶ መጥሪያውን ሊልክ ይገባ ነበር፡፡ ስለሆነም የተከበረው ፍ/ቤት ከላይ በተገለጸው አዋጅ መሰረት የስረነገር ስልጣን የለኝም በማለት መዝገቡን ዘግቶ ለሕግ ባለሙያ ያወጣነውን ወጪ በቁርጥ ወስኖ እንዲያሰናብተን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
Jan 13, 2025I have no idea but this group may help you https://t.me/what_does_the_law_say
Jan 13, 2025