ሰላም ። እንዴት ናችሁ? እኔ ብቻ ነኝ ግን ምንም የቤት ሞያ የሌለኝ? ካላችሁ እጅ አውጡ በፊት ምንም አይመስለኝም ነበር አሁን ላይ ግን አስፈላጊ life skill ,እንደሆነ ገብቶኛል። ከየት መጀመር እንዳለብኝም አላውቅም ምከሩኝ።
Jan 12, 2025በነገራችን ላይ ምንም መስራት ላይጠበቅብሽ ይችላል ግን ከእናትሽ ስር ወይም ከቤት ሰራተኛ ስር ማትጠፊ ከሆንሽ ልጅ እያለሽ ብዙውን ነገር አእምሮሽ መዝግቦ አስቀምጦታል... ለምሳሌ እኔ ከቤት የመጨረሻ ልጅ ነኝ ለዛም ይመስለኛል አንድም ስራ ሳልሰራ ነው ያደኩት ነገር ግን ከእናቴ ስር አልለይም ነበር አልፎ አልፎ ቡና ከመውቀጥ እና ከማፍላት በቀር መሶብ ራሱ ብከፍት ሩዋንዳ ነው ምታደርግብኝ እናቴ... ልክ ግን ከቤት እንደወጣሁ እና ወንደላጤ እንደሆንኩ የመጀመሪያ ምግብ የሰራሁት ፍርፍር ነበር እህል ቅጠል ማይል ፍርፍር ነበር ለዛውም ለጏደኞቼ ነው ያበሰልኩት 😂😂😂... ሙድ ተያዘብኝ አለፈ ... ሁለተኛ ቀን ያን ፍርፍር ደገምኩት ለማ ?ለፍቅረኛዬ... ገራሚ ሆኖ ነበር ከዛ ቀን አንስቶ ቢያንስ ለተከታታይ 3 ወይ 4 አመት ፍርፍር ሲያምራት ስራልኝ ነበር ምትለኝ... ታም ጎዝ ባይ.. ልጅ ወለድን በአጋጣሚ ኮሮና ላይ ነበር ማንም ቤት አይመጣም ብለን ዘጋን ለተከታታይ 3 ወራት እኔ ነበርኩ ያረስኳት ያልሰራሁትን የምግብ አይነት ጠይቂኝ .. ከገንፎ እስከአጥሚት ..ከቀይ ወጥ እስከቅቅል.. ከፓስታል ፉርኖ እስከ መንዲ(ሩዝ በዶሮ ስጋ) ስፕሪንግ ሮል ነሽ ክለብ ሳንዲዊች ነሽ ... የቀረኝ ነገር አልነበረም ሳላጋንን ... እና ምን ልልሽ ነው ልክ እንደ መስል ሜሞሪ ሁሉ ያየሽውን ኩኪንግ ስኪል አእምሮሽ ቀብሮ ይይዛ እሱ ፓንዶራ ቦክስ ሲሰበር እመኚኝ ዩ አር ኤ ሼፍ👩🏾🍳
Jan 12, 2025