Ere bftari yhe ayntla mibalw ngr ebakachu erdugn btam eyaskaygn nw 1amet tsebel nbrku tskayw eko maryamn
Jan 08, 2025እሺ የኔ እህት/ወንድም ለመዳን መጠመቅ ብቻ ትርጉም የለውም ኦርቶዶክስ ከሆንሽ/ህ ማድረግ ያለብሽን ልንገርሽ/ህ 1 ንስሀ መግባት ነው መንፈሶች እኛ ላይ ሚሰለጥኑት በሀጥያታችን ነው ንስሀ ከገባሽ አቅማቸው ይደክማል 2 ቂም ካለብሽ መተው ይህ ግዴታ ነው ለቂም የምንሰጠው ግምት አነስተኛ ነው ግን ጌታችንና መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ይቅር የማይልን ይቅር አይልም ፀሎትሽም በፍፁም አይሰማም 3 ፈጣሪን በፍፁም በየትኛውም መከራ አለማማረር ምነው ባልተፈጠርኩ አይነት አባባሎችን ከአፍ ፈፅሞ አለማውጣት ይህ ፈጣሪ እጅግ የሚጠላው ነው በመከራም መፅናትና ማመስገን ያስፈልጋል 3 ተጋድሎ ነው ይህ ሁሉም የሚከብደው ነው ግን ለማዳን የግድ ማድረግ ይኖርብሻል ለምሳሌ ፀሎት ስግደት ፆም(ከሀጥያትም ጭምር) ያስፈልጋል እነዚ ብዙ ሰው ሚከብደው ነገር ነው ግን ይህ እንዲቀልሽ የመናፍስትን ፈተና ማስቃሙ የተሻለው መንገድ ነው ያም ደሞ ልታስቆሚ ምትችዪው መቁጠሪያ ተጠቅመሽ በሰውነትሽ ላይ ያሉ መናፍስት ግንባር ላይ እንዲታሰር ማዘዝ ነው። ግንባር ላይ ከታሰሩ አንቺን መፈተን ማስጨነቅ ለፀሎት መከልከል ስገደት መከልከል አይችሉም። የመቁጠሪያ አጠቃቀም youtube ላይ ሰርች ብታረጊ ታገኛለሽ ግን መቁጠሪያ በአንገታችንና በእቻችን መጠምጠም አይቻልም መነኮሳት ብቻ ናቸው መቁጠርያ ማሰር የሚችሉት 4 ትህትና ነው። ይህ በሰዎች ብዙም ግምት ማይሰጠው ነው ግን አጋንንትን ለመጣል ከፀሎትም በላይ አደገኛ መሳሪያ ነው። ትህትና እራስን ከፍ ከፍ አለማድረግ በክፉ የመጣውን በደግ መመለስ ሰዎችን በትዕቢት አለማናገር እንዲሁም ሰዎችን አለማማት ፈጣሪ የሰዎችን ጉድ ደብቆ እኛ መግለጥ የለብንም ዝቅ ብሎ ቤተክርስትያንን ማገልገል ትህትና ነው ለምሳሌ የበረከት ስራ አለ ቤተክርስትያን ውስጥ ግቢውን እንኳን መጥረግ አምላካችንም የኛን ቆሻሻ ይጠርግልናል ትህትና አጋንንትን እንዴት ሊያሸንፍ ይችላል ልትዪ ትቺያለሽ ግን የሚመጣብን መከራ ሁሉ እኛን ለመንግስተ ሰማያት የሚያበቃ ሀይማኖት ውስጥ እንድንገባ ታቅዶ ነው ፈጣሪ ትሁት እንድንሆን ይፈልጋል አንድ የምነግርሽ ነገር ቢኖር የሚያድነን ፈጣሪያችን ምህረት ይገባዋል ሲል እንጂ ፀሎታችን ወይንም ስግደታችን ወይም ፀቀሉ አደለም ስግደቱ ለጌታ መገዛትሽን በማሳየት ከፈጣሪ ምህረት የምታገኚበት በመፀለይሽ ለፈጣሪሽ ጊዜ በመስጠትሽ ምህረት የምታገኚበት ነው ስለዚ በመጠመቅ ብቻ የፈጣሪን ምህረት ማግኘት አይቻልም ይህን ካደረግሽ ፈጣሪ ምህረት ላያደርግልሽ አይችልም በተለይ ትሁት ልብ አምላክን ይስበዋል ከዚ ከዚ ውጪ መተት ካለብሽ ሰዎች እያደሱብሽ ምትቸገሪ ከሆነ ብዙ ቃል ኪዳን ያላቸው ገዳማት አሉ ቦታውን በመርገጥሽ ብቻ ተሀድሶ የሚያቆም ቃል ኪዳን ያላቸው ገዳማት አሉ የሚቀርብሽ ጋ መሄድ ነው እኔ ከአዲስ አበባ 100 km ሚርቅ ገዳም አቃለው ተሀድሶ ያቆማል ምትፈልጊው ከሆነ ጠይቂኝ እጠቁምሻለው ወይም እጠቁምሀለው
Jan 08, 2025