ሰላም እህት ወንድሞቼ እንዴት ናችሁ እባካችሁ ልትፈርዱብኝ ሳትቸኩሉ ሃሳብ ስጡኝ አስበንበት ባልሆነ ሰአት ከሆነ ልጅ ጋር ሴክሹዋል ነገር ጀመርን። በወቅቱ እኔም እሱም ፍቅረኛ ነበረን እኔ ግን ልጎዳው ስለማልፈልግ ከዚ በላይ ብዬ ከፍቅረኛዬ ጋር ተለያየን። ከዚህኛው ልጅ ጋር ያለኝን ነገር ግን ማቆም አልቻልኩም። ከጎኔ ተኝቶ ከፍቅረኛው ጋር ሲያወራ ምን ያህል ጨካኝ ሴት ብሆን ነው ለሷ እንኳን የማላዝነው እያልኩ በራሴ በጣም አፍራለው። ለመለየት ሞክሪያለው ግን እመኑኝ እርቀዋለው ብዬ ሳስብ ጭራሽ ቀርቤው አገኘዋለው እራሴን። እሱ ጋር ስሄድ 2 ስሜቶችን ነው የማስተናግደው አንደኛው ሰላም ይሰማኛል ሁለተኛው ግን እሱ ጋር ስሄድ ኮንፊደንሴን አጣለው፣ ለራሴ ያለኝ አመለካከት ይወርዳል። ኢቭን የማውቀውን ነገር እሳሳታለው እና እራሴን እንደ ደደብ ነው እዛ ጋር የምቆጥረው። ለምን እራሴን መቆጣጠር እንዳልቻልኩ አላውቅም። ከሴክስ ጋር ብቻ አታያይዙት ኢሞሽናሊም ቢሆን በጣም አታችድ ሆኛለው። እባካቹ ለመስደብ እና ለመፍረድ እንዳትሮጡብኝ፣ እኔ እራሴ ህሊናዬ የሚወቅሰኝ ይበቃኛል ግን እስኪ ለእኔ ለእህታቹ እንዲ ሞክሪ ብላቹ ሃሳብ ሥጡኝ። እና ሌላው የረሳሁት ክብረ ንጽህናዬንም የሰጠሁት ለሱ ነው። ለዛ ይሆን እንደዚ ከሱ መለየት ተራራን መግፋት ያህል የሆነብኝ
Jan 08, 2025lol. leave him the way you left your boyfriend. Can't say anything positive other than this without judging
Jan 08, 2025