በጣም እምወደው ፍቅረኛ ነበረኝ። እና አብረን ካፌ ውስጥ ስንቀመጥ ብዙ ሴቶች ላይ ይፈዛል። ደሞ በግልፅ ነው እሚያወራው.. like "ወይኔ ስታምር!!!" እያለ ልቡን በእጁ ይደግፋል። እኔ ደሞ የምር ይከፋኝ ጀመር። እሱ ፊት ምንም ተናግሬው አላውቅም። ምክንያቱም መልሶ እኔን ነው gaslight እሚያረገኝ እና ጨቅጫቃ እሚለኝ። ግን በቃ ከጊዜ ወደጊዜ insecure እየሆንኩ መጣሁ። ራሴን መጥላት ጀመርኩ፣ ቆንጆ ሴት ባየሁ ቁጥር እሱ አያት አላያት እያልኩ መሸማቀቅ ጀመርኩ። መቼስ ቆንጆ እማይወድ ሰው የለም.. የሱ ግን ተጋነነ በቃ ቆንጆ ሲያይ እንደሆነ ነገር ነው እሚያረገው። እና በመጨረሻም ተለያየን። ግን አሁንም ያ Trauma ሊለቀኝ አልቻለም በቃ insecure ሆኜ ቀረሁ። tiktok ላይ እንኳን ብዙ ቆነጃጅት ሲመጡ ወድያው ነው ማሳልፈው or Accountኣቸውን block አረገዋለሁ። አእምሮዬ ታሟል ምን እንደሚሻለኝ አላውቅም😔
Jan 07, 2025ዞር በይ ወደዛ በጥፊ ነበር ማጠናግረው የኔ ፍቅረኛ ቢሆን ያውቃል ምን እንደማረገው. ራስ መተማመንሽ እና ለራስ ክብር ላይ መስራት አለብሽ. መጀመሪያ አንቺ ራስሽን ማወዳደር የለብሽም. ሁለተኛ ነገር አንቺ አምላክ በምስሉ ቆንጆ አረጎ በፈጠረሽ አንቺ ማን ስለሆንሽ ነው ራስሽን ምትንቂው? ሶስተኛ ነገር ሁሉም ሰው ቆንጆ ነው ግን ጎልቶ እንድታይ ምያረገው ብር ነው (Gym, ሽቶ, face care routine, አለባበስ, ራስ እንክብካቤ, makeup, human hair, eyelash, artificial nail...)ያለውንም በተፈጥሮ ራሱ ለመጠበቅ ብር ያስፈልጋል ለዛ እሱ ላይ አተኩሪ. ሌላ ጊዜ ወንድ ፊት ለፊትሽ ሲላከፍ አንቺም እንደሱ ተላከፍዬ ወይኔ 6 pack ሲያመር, ወይኔ ጡንቻው, ወይኔ ትከሻው ስፋት,ድምጹ ሲያምር,አቤት ግርማ ሞገሱ, ወንዳ ወንድ ነው ከዛ እንዴት እንደ ሚሆን እይው.ከዛ በሁዋላ ከደገመው ያ ያንቺ ሰው አይደለም ምክንያቱም አጋጣሚውን ካገኘ አይኑን አያሻም
Jan 07, 2025