ፍቅረኛ አለችኝ በጣም የምወዳት እና እኔ ለፍቅራችን ሁሉንም ነገር ላረግ እችላለሁ ግን እስዋ እንገናኝ ስላት እቤት አይመቸኝም family ጋ አዛ ነው ነው የምትለኝ ። እኔ ደሞ ከ እስዋ በጣም ትልቅ ፍቅር ነው የያዘኝ እኔ ። ለምን እንደዛ እንደምትል በጣም ነው ግራ የገባኝ ምክንያቱ የጎደለ ነገር ይኖራል እንዳልል እኔ አሁን ላይ financial stable ነኝ ሁሉም ነገር አለኝ ማለት እችላለሁ በዚህ እድሜየ ለእስዋ ሁሉንም ነገር ላረግላት እችላለሁ ። even እንገናኝ የምላት ብታምኑም ባታምኑም አብረን ቁጭ ብለን ከልባችን እንድናወራ ነው የምፈልግ እንዲህ ያልኩት ደሞ ምን አልባት ሁሌ እንገናኝ ስላት ለsex አይደለም ምክንያቱም ለsex ግዜ ገና ነው ብዬ ስለማምን አሁን ላይ ያለ እስዋ ፍላጎት ምንም ነገር ማረግ አልፈልግም ምክንያቱም በጣም ነው የምወዳት ። ችግሩ ከኔ ከሆነ ብየ ግዜ የማንሰጣጥ ከሆነ ይብቃን ስላት እኔ እኮ በጣም ነው የምወድህ ትለኛለች so guy's what is you ምክር for this situation
Jan 07, 2025ራስህን በርሷ ቦታ አድርገህ አስብ። ስለቆሸሹ ወንዶች ብዙ ነገሮችን ከሰማች በኋላ ዛሬ አንተ መጥተህ ለክፉ አልፈልግሽም ብትላት እንዴትስ ትመንህ? Stable ከሆንክና ከትዳር በኋላ የማትጉላሉ ከሆነ አግብተሃት ፍቅርህን ለርሷ ብቻ ሳይሆን ለአለም አስመስክር። በዚያ ላይ ደግሞ እውነቷን ቢሆንስ? አንዳንድ ቤተሰቦች ያለንበትን ተጨባጭ ስለተረዱ ሴት ልጆቻቸው ላይ በጣም ነው የሚያጠብቁት። እርሱን ትተን እኔ እንኳ ለ8ኛ ክፍል ወንድሜ ነጻነት የተሞላበት ከባድ ቁጥጥር ነው የማደርግበት። ስለዚህ አትፍረድባት። ሌላው ደግሞ አንተ ሴት ልጅ ብትኖርህ ያላንተ ፈቃድ ከአንድ ጎረምሳ ጋር ለብቻዋ እንድትውል ትፈቅድላታለህ? በራስህ ሳይሆን ያን ጎረምሳ እንደማታውቀው ሆነህ አስበው። ደግሞ ወንድ ልጅ ከሴት አጠገብ ተቀምጦ ለወሲብ ባይጋበዝ እንኳ ለወሲብ እሩብ ጉዳይ የሆኑ ነገሮችን መስራቱ መች ይቀርለትና! ሐሳብህ ውድቅ ነው። አያስኬድም።
Jan 07, 2025