ሰላም ለሁላችሁ እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን!!! አንድ ነገር ላማክራችሁ በተለይ የህግ ባለሙያዎች ካላችሁ እንዲሁም በተለምዶ እዉቀተ ካላችሁ:- አባቴ ካረፈ 6 ወራቶች አለፉ ነገር ግን አባቴ እኔን ጨምሮ ሌላ 4 ልጆች አሉት ከ 2ቱ ጋር በእናት አንገናኝም አባቴ ባረፈ በ 6 ወራት ጊዜ ዉስጥ በእናት የማንገናኘዉ ወንድሞቼ በጣም የበሀሪ ለዉጥ አመጡ በአጠቃላይ የኛን እናት ነዉ የሚወቅሷት ብቻ በዚም ሆነ በዚያ ያለዉን ዉርስ ለመሸጥ እና ለመካፈል ነዉ የሚፈልጉት ነገር ግን አሁን ላይ እናንተ የ አባት ድርሻ ብቻ ነዉ የምትወስዱት አሉን እኔ እና ታላቅ እህቴን ግራ የገባኝ ነገር ያለዉ ንብረት በሙሉ በአባታችን ነዉ ነገር ግን እነሱ የኛም እናት አለችበት ይላሉ ነገሩን ሳይባባስ ባዉቅ ጥሩ ነዉ ብዬ ነዉ እርግጥ ነዉ አሁን የምንኖርበትን ቤት አባታችን ከእነሱ እናት ጋር ኖሮበታል ነገር ግን ሙሉ በሙሉ በ አባታችን ስም ነዉ ያለዉ እና እንዴት ነዉ ሙሉ በሙሉ የመካፈል መብት አለን ወይስ ግማሹን ማለትም የአባት ተብሎ ነዉ የሚሰጠን ለእኔ ና ለእህቴ ? አመሰግናለዉ ለመልካም ምላሻችሁ
Jan 06, 2025Get professional advice from lawyer here https://t.me/what_does_the_law_say
Jan 07, 2025