ጋይስ 200 ካሬ ላይ ያረፈ ቤት አለኝ እና ቤቱ ከ2.5M እስከ 3M ዋጋ ያወጣል እና አሁን ላይ በ4M ብር የሚሸጥ ቤት ተስማምቼ ጨርሼ ነበር ግን እጄ ላይ 2M ብር ብቻ ነው ያለኝ እና ያሁኑን ቤቴን አሲዤ ባንክ 2M ያበድረኝ ይሆን? እርግጠኛ ነኝ ከእግዚአብሔር ጋር በ1አመት ውስጥ 2ሚልዮን ብሩን ከነወለዱ እከፍላለሁ ግን እንዴት ነው ይሄን ብድር ከባንክ ማግኘት የምችለው? የምታቁትስ የሚያበድር ባንክ የትኛው ነው?እባካችሁ ተባበሩኝ ቤቱን ላጣው አልፈልግም 🙏🙏🙏
Jan 06, 2025ማበደሩንስ ያበድርሃል። ንግድ ባንክ እያበደረ እንደሆነ አውቃለሁ። ሌሎች ጀምረው እንደሆነ አላውቅም። ሂደቱን ትንሽ ልበልህ.. የፋይናንስ ጥያቄ ማመልከቻ፣ የፋይናንስ ጥያቄ ፎርም ትጽፋለህ። እነርሱም ከተባበሩህ ይጽፉልሃል። ማንኛውም የታደሰ መታወቂያ ታቀርባለህ። ልታስዪዘው የፈለግከው ቤት ህጋዊ መረጃዎች ሁሉ መሟላት አለባቸው! የግንባታ ፈቃድ፣ የህንጻ ፈቃድ ይሟሉ። ቤቱ የሊዝ ነው ወይስ የሊዝ ያልሆነ? የሊዝ ከሆነ በየአመቱ የሚከፈለውን የሊዝ ክፍያ የከፈልክበት ደረሰኝ ማዘጋጀት (ሊጠይቁህ የሚችሉት የ2016 እና/ወይም የ2017 ነው) የግል ከሆነ የአፈር ግብር (ካልረሳሁት) የከፈልክበት ደረሰኝ ታዘጋጃለህ። (tax clearance) የቤትህን ፕላን እና የቤቱ ብሉ ፕሪንት ታዘጋጃለህ። ባለትዳር ካልሆንክ ያላገባ ሠርተፊኬት ከቀበሌህ ታጽፋለህ። (Usually ለ6 ወር ነው የሚያገለግለው። ካለፈበት ታድሰዋለህ።) ባለትዳር ከሆንክ የጋብቻ ሠርተፊኬት (+ የጋራ ቲን ነምበር) ይፈለጋል። የባንክ ስቴትመንት ትጠየቃለህ። አሪፍ ብር እንዲሰጡህ ከፈለግክ አካውንቶችህ በአሪፉ የብር ትራንዛክሽን ሊኖራቸው ይገባል። አለዚያ ቤትህ 10,000,000 ቢያወጣ እንኳ 1,000,000 ላይሰጡህ ይችላል። የምትጠቀማቸው ባንኮች ሁሉ ስቴትመንት ማቅረብ ትችላለህ። የሚጠይቁህም የሁሉንም ባንኮች ነው። ባንኮቹ ጋር ስቴትመንት ለመጠየቅ ስትሄድ "ለኮላተራል የሚሆን የ1 አመት ስቴትመንት ስሩልኝ" ነው ማለት ያለብህ። ተራ ስቴትመንትና የኮላተራል ስቴትመንት ይለያያል። የኮላተራሉ ስቴትመንት ላይ ማኅተም መመታቱን አረጋግጥ። TIN Number, የንግድ ምዝገባ የምስክር መረቀት፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ ፋይናንሺያል ስቴትመንት፣ ቢዝነስ ፕላን፣ Financial statement, Business plan, Cash flow ይሟሉ። ለጊዜው የማስታውሰው ይህን ነው።
Jan 07, 2025