ከድንግልና ጋር አንድ የኾነ ሐለብ በሩካቤ ሳይሆን በብሥራት እንደ ንብ ከሆድ መጥበብ ጋር የመለኮት ስፋት አንቺ ኾነሽ ሳለ ታናሿ ሙሽሪት ወዳንቺ የመጣው በሩካቤ ሳይሆን በብሥራት እንደ ንብ ከሆድ What does this mean እንደ ንብ
Jan 04, 2025አበው ቅዳሴ ማሪያምን ሲተረጉሙ እንደ ንብ ያለ ሩካቤ የሚለውን ሲፈቱት ቃል በቃል ምን ይላል፦ ሐተታ" ይህ ንብ አውራው ድምጽ ባሰማው ጊዜ እንበለ ዘርዕ እጭ ሰርቶ ያድራል ከመ ንህብ እለ ወተአነዝር እግዝእቶን ለአንህብት እንዲል።" ከቃል ድምጽ የተገኘ ፅንስ ይለዋል አባ ሕርያቆስ ጌታችን የመጸነሱን ነገር ሲያስብ. . . የመላኩ ገብርኤልን ቃል ሰምታ እንደ ቃልህ ይደረግልኝ ባለች ቅጽበት በማህጸኗ ያ አካላዊ ቃል ተቀርጿል. . . ቃልን በመስማት ያለ ወንድ ዘር መጸነሰ ራሱ በደንብ ከታሰበበት በጣም ያስገርማል. . . እመቤታችንን ልዩ የሚያደርጋት የሰማችው ቃል በዘጠነኛው ወር መልክ ይዞ በማየቷ ነው. . . እሱ ብቻ አይደለም ፈጣሪዋን መሆኑ ከሰው ልጆች ልዩ ያደርጋታል. . . አባ ሕርያቆስም ይሄ ነገር ድንቅ ሆኖበት በመንፈስ ቅዱስ የደረሰው ቅዳሴ ሰርክ አዲስ በመሆን ሁሌም ሲሰሙት ሲያነቡት ሰዎች የተለየ መንፈሳዊ መነካት እንዲሰማቸው አድርጓል
Jan 04, 2025