Le orthodox becha ሰላም ሰዎች ስለ ቅዱስ ቁርባን ጥያቄዎች ነበሩኝ 1, አንድ ሰው ከንስሃ በኋላ ቁርባን መቀበል አለበት! ግን ቀኖናውን በፍጹም ጸጸት እና መመሰጥ ካልፈጸመ መቁረብ ይችላል? ይህን ያልኩበት ምክንያት ቁርባን አንዱ ኃጢአት ማስተሰረያ መንገድ ስለሆነ ነው ስለዚህ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለ ቢቆርብ ኃጢአት ይሆንበታል ወይስ ኃጢአቱን እንዳይሰራ ብርታት ይሆነዋል? በቻላቹት አቅም በተለይ ዕውቀቱ ያላቹ ብትመልሱልኝ ደስ ይለኛል🙏
Jan 01, 2025ስጋ ወደሙ የንስሐ ማሰሪያው ነው ንስሐ ማለት ደግም መጸጸት ማለት ነው ስለ በደልነው ነገር ከልብ ሳንጸጸት ቀኖናውን መፈጸም አይቻልም ምክንያቱም ቀኖናው የሥራ ሳይሆን የጸጸት ነው። ለማንኛውም የራስህን የንስሐ አባት ጠይቃቸው አባት እስካለህ ድረስ ራሳቸውን ማማከር እንጂ እስኪዚህ መቸገር አልነበረብህም
Jan 01, 2025